Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ግንቦት 12፣ 2015 8ኛ ትምህርት
የእግዚአብሔር የፍቅር ቀን የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ሰንበታቴንም ቀድሱ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ መካከል ምልክት ይሆናሉ።” (ሕዝ 20፡20)።
ለንባብ የተመረጠዉ፡   Child Guidance, pp. 527–537 
እግዚአብሔርም ሰንበት ለሰው ልጅ በገነት እንኳን አስፈላጊ መሆኑን ተመለከተ። የግል ፍላጎቱንና ምኞቱን ከሰባቱ ቀናት በአንዱ እንኳ ሊተውና ወደ እግዚአብሔር ሊመለከት፣ ሥራውንና መልካምነቱንም ሊያደንቅ ይገባል። ሰው አለኝ የሚለው ነገር ሁሉ ከፈጣሪው እጅ የመጣ ነውና ስለዚህ ፈጣሪውን ያስታውስ እንዲሁም ምስጋና ያቀርብ ዘንድ የሰንበት ቀን ያስፈልገዋል።” —አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 48.

1. የዘላለም ሕይወት እሁድ ግንቦት 06
ሀ. ወደዚያች የተሻለች ምድር የመሄድ መብት ስላላቸው ብቻ ምን ማስተዋል አለብን? ራእይ 22:12-14፤ ያእቆብ 2፡10 [ብዙዎች]አንዳንዶቹን የጌታ ሕጎች ለማመንና ለመታዘዝ እየተቃወሙ መደበኛውን ኃይማኖታዊ አገልግሎት የሚካፈሉ አሉ፡፡ ለእንዲህ ዓይነቱ አገልግሎት የእግዚአብሔር መንፈስ ምላሽ የለውም፡፡ ሰዎች የቱንም ያህል የተሟሟቀ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ቢፈጽሙና አንዱን ትእዛዝ ግን እያወቁ የሚጥሱ ከሆነ ጌታ ሊቀበላቸው አይችልም፡፡”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 634. ለ. በዚህ ህግ ምን እየሰራን ነው እና የት ነው መቀመጥ ያለበት? 2ኛ ቆሮንቶስ 13:5፤ ዕብራውያን 8፡10 ባህሪያችንን ከማይሻረው የእግዚአብሔር ህግ መለኪያ ጋር ማወዳደር አለብን። ይህንን ለማድረግ ሥራችንን በአምላክ ቃል ለመመዘን ቅዱሳን ጽሑፎችን መመርመር አለብን።”—The Review and Herald, February 14, 1893.

2. የተተነበየው ተሃድሶ (RESTORATION) ሰኞ ግንቦት 07
ሀ. የአምላክ ሕዝቦች ለአሥርቱ ትእዛዛት ለሥነ ምግባራዊ ሕጉ ልዩ አክብሮት እንደሚኖራቸው የሚያሳየው የትኛው ትንቢት ነው? ኤርምያስ 6:16፤ ኢሳያስ 58:12 በመጨረሻው ዘመን እያንዳንዱ መለኮታዊ ድርጅት መታደስ አለበት። በሰው የተቀየረው የሰንበት ስብራት መጠገን አለበት። የእግዚአብሔር ቅሬታ ሕዝብ በዓለም ፊት እንደ አዳሾች ሆነው ይቆማሉ። የእግዚአብሔር ሕግ የእድሳት ሁሉ መሠረት መሆኑን ይመሰክራሉ። አራተኛው ትዕዛዝ የሆነው ሰንበት የፍጥረት ማስታወሻ መሆኑንና የእግዚአብሔርን ሀይል ያለ ማቋረጥ የሚገልጽ ሐውልት መሆኑን ያውጃሉ። ግልጽ በሆነ ምስክርነት አሥርቱ ትእዛዛት ሙሉ በሙሉ መከበር እንዳለባቸው ያስተምራሉ። በክርስቶስ ፍቅር ተገፋፍተው የፈራረሱትን ቦታዎች ለመጠገን ከእርሱ ጋር መተባበር አለባቸው። ሰባራውን ጠጋኝ የመኖሪያ መንገዱን አዳሽ ናቸው።”—ነቢያትና ነገሥታት፣ ገጽ. 678(457) ለ. በዚህ ተሐድሶ (RESTORATION) ውስጥ ሊታሰብበት የ ሚገባውን ልዩ ነጥብ ይጥቀሱና ውጤቱን ያብራሩ። ኢሳይያስ 58:13, 14 ሰንበት ሲገባ፣ ለራሳችን፣ ለድርጊታችንና ለቃላታችን ጥበቃ ማድረግ አለብን፣ ይህም የጌታን ጊዜ ለራሳችን ጥቅም በማዋል እግዚአብሔርን እንዳንሰርቅ ነዉ። ለመተዳደሪያነት የምንሠራዉን የራሳችንን ስራ ወይም በስድ ስቱ የስራ ቀናት ሊደረግ የሚገባዉን ማንኛውንም ነገር ራሳችን ልንሰራ ወይም ልጆቻችንን እንዲሰሩ መፍቀድ የለብንም። አርብ የዝግጅት ቀን ነው። ከዚያምለሰንበት አስፈላጊውን ዝግጅት ለማድረግና ስለእርሱ ለማሰብና ለመነጋገር ጊዜ ሊመደብ ይኖርበታል። በሰማይ ፊት ቅዱስ ሰንበትን እንደ መጣስ የሚቆጠር ምንም ነገር በሰንበት ቀን ሊነገር ወይም ሊደረግ አይገባም። እግዚአብሔር የሚፈልገው በሰንበት ከሥጋዊ ድካም እንድንርቅ ብቻ ሳይሆን አእምሮ በቅዱስ ነገሮች ላይ እንዲያተኩርም ጭምር ነው። አራተኛውን ትእዛዝ በዓለማዊ ነገሮች ዙሪያ በመነጋገር ወይም በቀላልና በማይረባ ውይይቶች ላይ በመሳተፍ እንተላለፋለን።”—Testimonies for the Church, vol. 2, pp. 702, 703.ሰንበትን የክርስቶስ የመፍጠርና የማዳን ኃይሉ ምልክት አድርገው ለሚቀበሉት ሁሉ ያስደስታቸዋል። በሰንበት አማካይነት ክርስቶስን ስለሚያዩት በእርሱ ይደሰታሉ። ሰንበት የፍጥረት ሥራ ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ትልቅ ኃይል እንዳለው ማስረጃ መሆኑን ያመለክታቸዋል። በኤደን የታጣውን ሰላም ለማስታወስ ሲረዳ በአዳኛችን አማካይነት ስለሚታደሰው ሰላም ይነግረናል።—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 289(285)

3. የሰንበት ተሐድሶ ማክሰኞ ግንቦት 08
ሀ. እግዚአብሔር ሕዝቡ ስለሰንበት ያላቸውን አመለካከት ለማስተካከል የፈለገው እንዴት ነው—እና ሰንበትን አለመቀበላቸዉን ቢቀጥሉ ምን ይሆናል? ኤርምያስ 17:24-27 አንድ ጊዜ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመከተል ከከተማው ዋና በሮች በአንዱ ላይ ቆሞ በመከተል ከከተማው ዋና በሮች በአንዱ ላይ ቆሞ ሰንበትን የማክበርን ዋናነነት አጥብቆ ተናገረ። የኢየሩሳሌም ኗሪዎች የሰንበትን ቅዱስነት (ቅድስና) መዘንጋት ጀምረው ነበር። በሰንበት ቀን የዕለት ተግባራቸውን እንዳያካሂዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶአቸው ነበር።. . .ስለዚህ በሕጉ መጽሐፍ የሠፈረውን ትዕዛዝ ተከትለው በትክክል ለመኖር የተሰጠውን ሥነ ሥርዓት የሕይወት መመሪያ ነቢዩ አጥብቆ አስተማረ። ነገር ግን የይሁዳ ሁኔታ ከአሳሳቢ ደረጃ ላይ ስለደረሰ፣ የተሻለ ለውጥ ለማስገኘት ከባድ እርምጃ መወሰድ ነበረበት።”—ነቢያትና ነገሥት፣ ገጽ 411, 412 ለ. ተመሳሳይ ድርጊቶች ተመሳሳይ ውጤቶችን እንዴት ይፈጥራሉ? 1ኛ ቆሮንቶስ 10:5, 6 አምላክ ተለውጧልን? ሚልክያስ 3:6; ዕብራውያን 13፡8 [የአንድ ነገር] ምንጭ (መንስኤ) ባለበት ሁሉ፣ ተመሳሳይ ውጤቶች ይከተላሉ። ከዝንባሌዎቹ ጋር ስለሚጋጭ ለሃላፊነቱ ያለውን መሰጠት ሆን ብሎ የሚገድብ እርሱ በስተመጨረሻ በእውነትና በስህተት መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት የሚያስችለውን ኃይል ያጣል። ማስተዋሉ ይጨልማል፣ ህሊናው ይደንዛል፣ ልቡ ይደነድናል፣ ነፍሱም ከእግዚአብሔር ትለያለች። መለኮታዊ የእውነት መልእክት ተቀባይነት ባጣበት ወይም በቀለለበት በዚያ ስፍራ ቤተ ክርስቲያን በጨለማ ትጀቦናለች፤ እምነትና ፍቅር ይቀዘቅዛሉ፤ መቃቃርና አለመግባባት ይከተላል። የቤተ ክርስቲያን ምዕመናን መሻቶቻቸውንና ኃይላቸውን ዓለማዊ ነገሮችን በማሳደድ ላይ ማእከል ያደርጋሉ፤ ኃጢአተኞችም በአልፀፀት ባይነታቸው ይደነድናሉ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 378፣ 379“ዛሬ ሰይጣን ተመሳሳይ ክፋቶችን ለማስተዋወቅ እየተጠቀመበት ነው፣ ጥረቱም በእስራኤል ዘመን ብዙዎችን ወደ መቃብራቸው የመራቸዉን ዓይነት ተመሳሳይ ውጤት እያስከተለ ነዉ።”—The Review and Herald, February 4, 1909.ዛሬም የአምላክን ሕግ ጠባቂ ነን በሚሉት ሰዎች መካከል ተመሳሳይ አደጋ አለ። ትእዛዛትን የሚይዙበት አክብሮት ከመለኮታዊ ፍትህ ኃይል ሊጠብቃቸው እንደሚችል እራሳቸውን ለማሞካሸት ይቸኩላሉ። ለመገሠጽ (ሲገሰጹ) ፈቃደኞች አይደሉም፣ እና ኃጢአትን ከሰፈሩ ለማራቅ በጣም ቀናተኛ ሆነዉ የሚሠሩትን የአምላክ አገልጋዮች ተጠያቂ ያደርጋሉ።”—The Signs of the Times, February 12, 1880, Art. B.

4. ችግሮች ረቡዕ ግንቦት 09
ሀ. ሰንበት ከሲና ተራራ በፊት እንደነበረ እን ዴት እናውቃለን? ዘጸአት 20:8፤ 16:4, 5 ዕብራውያን ይህንኑ ሕግ ቸልተኝነት ያሳዩት እንዴት ነው? ዘጸአት 16፡27-30 እስራኤላውያን በምድረ በዳ በነበራቸው ረጅም ጉዞ በየሳምንቱ በሚያደርጉት ጊዜያዊ ቆይታ የሰንበትን ቅዱስነት እንዲያስተዉሉ ለማድረግ በዕለቱ ሦስት እጥፍ ተዓምራቶችን እንዲታዘቡ ይደረጉ ነበር። ከወትሮዉ እጥፍ መጠን ያለዉ መና በስድስተኛዉ ቀን ሲወርድላቸዉ በሰንበት ቀን ግን አንድም አይኖርም። ለሰንበት ቀን የሚያስፈልጋቸዉ መጠን ጣፋጭና ንጹህ ሆኖ ይቆያቸዉ የነበረ ሲሆን፤ ነገር ግን በሌሎቹ የሳምንቱ ቀናት በዕለቱ የሰበሰቡትን መና ለቀጣዩ ቀን ቢያስቀምጡ ይበላሽባቸዉ ነበር።ለእስራኤላዊያኑ ይወርድ ከነበረዉ መና በተያያዘ መመለከት እንደምንችለዉ አንዳንዶች እንደሚሉት ሰንበት የተቋቋመዉ ትዕዛዛቱ በሲና በተሰጡ ጊዜ አልነበረም። እስራኤላዊያን ወደ ሲና ከመምጣታቸዉ አስቀድሞ ሰንበት በእነርሱ ላይ አስገዳጅነት እንዳለዉ አስተዉለዋል። ሰንበት ዝግጅት ሲያደርጉ አርብ ዕለት እጥፍ መሰብሰባቸዉና በነጋታዉ ከሰበሰቡት አንዱም ተበላሽቶ አለመጣሉ፤ ቅዱስ የሆነዉ የእረፍት ቀን ተፈጥሮ ያለማቋረጥ በአዕምሮአቸዉ ተጽዕኖ አድርጎባቸዉ ነበር። ከሕዝቡም አንዳንዶቹ መና ሊሰበስቡ በሰንበት በወጡ ጊዜ ጌታ ፡- “ትእዛዜንና ሕጌን ለመፈጸም እስከ መቼ እምቢ ትላላችሁ?” ሲል ሙሴን ጠየቀዉ።”—አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 331 (1) ለ. በምድረ በዳ በተላይ ከሰንበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ያጋጠማቸዉ ችግር ነበር ወይ? አብራሩ። ሕዝቅኤል 20:10-13 አርባ ዓመት በፈጀው አጠቃላዩ የምድረበዳ ጉዞ፤ በተአምር ይወርድላቸው በነበረው መና አማካኝነት ሕዝቡ ስለ ሰንበት ቅዱስ ግዴታ በየሳምንቱ በተለየ መንገድ እንዲያስታውስ ይደረግ ነበር። ነገር ግን ይህም ወደ መታዘዝ አላመጣቸውም። ምንም እንኳ በአራተኛው ትእዛዝ ዙሪያ ቀደም ሲል የተጣለው ዓይነት ከባድ ቅጣት የሚጠይቅ ግልጽና በድፍረት የተሞላ መተላለፍ ባይፈጽሙም ነገር ግን ግዴለሽናትና ቸልተኝነት ይስተዋልባቸው ነበር። “ሰንበቴንም ፈጽመው አረከሱ” (ሕዝ. 20፡ 13-24)፡፡ የመጀመሪያው ትውልድ ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዳይገባ ከተከለከለባቸው ምክንያቶች አንዱ ይኸው ነው፡፡ ያም ሆኖ ልጆቻቸው ትምህርት አልወሰዱም፡፡ አርባ ዓመት በፈጀው ጉዞአቸው ምንም እንኳ ወደ ከነዓን እንዳይገቡ እግዚአብሔር ባይከለክላቸውም ነገር ግን በተስፋይቱ ምድር ከሰፈሩ በኋላ በአረማውያን መካከል ተበታትነው እንዲኖሩ አዘዘ፡፡”—ኢቢ. ገጽ 409፣410።

5. ጠቃሚ ትርጉም ሐሙስ ግንቦት 10
ሀ. የሰንበት ትእዛዝ አዲስ ትእዛዝ አለመሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? ዘጸአት 20፡8-11 ሰንበት በፍጥረት ወቅት የተሰጠ ትእዛዝ እንደሆኑ በዐሥርቱ ትእዛዛት ላይ እንደ አዲስ አልቀረበም፡፡ ሰንበት ፈጣሪ ለሠራው ሥራ እንደ ማስታወሻ የሚታሰብና የሚከበር ዕለት ነው፡፡ ሰንበት የሰማይና የምድር ፈጣሪ እግዚአብሔር መሆኑን በማመላከት እውነተኛውን አምላክ ከሐሰተኛ አማልክት ለይቶ ያስቀምጣል፡፡ ሰባተኛውን ቀን ሰንበት የሚጠብቁ ሁሉ ያህዌን እንደሚያመልኩ በድርጊታቸው ያሳያሉ፡፡ በመሆኑም ሰንበት በምድር ላይ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሰዎች እስካሉ ድረስ ለእርሱ ያላቸው ታማኝነት ምልክት ነው፡፡” —አበዉና ነቢያት፣ ገጽ. 307. ለ. ዋናውን ትእዛዝ ከየት እናገኛለን እና ይህ የሰንበት ተቋም ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ህዝብ ምን ትርጉም አለው? ዘፍጥረት 2:1-3ሕዝቅኤል 20፡20 በፍጥረት ወቅት እውን የሆነው የሰንበት ቀን አንዱ አካል የሆነው የፍጥረት ሣምንት፤ እነሆ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ተጠብቆ ቆይቶአል፡፡ እግዚአብሔር እራሱ አንዱን ሳምንት ለክቶ፤ ያንን ተከትለው ለሚጡት ዘመናት እንደ ናሙና ሰጠ፡፡ የፍጥረት ሣምንት ሰባት ቀናት ከሚይዘውና ዛሬ አንድ ሣምንት ብለን ከምንጠራው ጋር እኩል ነው፡፡ የፍጥረት ሥራ ስድስት ቀናትን ሲወስድ በሰባተኛው ቀን ግን እግዚአብሔር ከሠራው ሥራ በማረፍ ዕለቱን ባረከው፤ ለሰው ልጆች የዕረፍት ቀን አድርጎም ለየው፡፡”—ኢቢ . 111.እግዚአብሔር በሰንበት ቀን ስላረፈ «ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም» ማለትም ለተቀደሰ ተግባር ለየው። ይህን ቀን እግዚአብሔር ለአዳም የእረፍት ቀን አድርጐ ሰጠው። ሰንበት የፍጥረት ሥራ መታሰቢያ ስለሆነ የእግዚአብሔር ኃይልና ፍቅር ምልክት ነው።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 281(276)

የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ግንቦት 11
1. በዘላለም ሕይወት እና በአስሩ ትእዛዛት መካከል ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? 2. በሰንበት ጉዳይ ላይ ከተነገረው ተሐድሶ ምን እንማራለን? 3. በጊዜያችን፣ እንደ ኤርምያስ ዘመን ተመሳሳይ የላላ አቀራረብ መኖሩ የሚያስከትላቸው ውጤቶች ምንድን ናቸው? 4. በምድረ በዳ ሰንበትን አለማክበር ምን ያህል ተስፋፍቶ ነበር እና ውጤቱስ ምን ነበር? 5. የሰንበት ቀን ለእርስዎ በግል ምን ትርጉም አለው?
 <<    >>