Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ በፖርት ሞርስቢ ውስጥ ላለው የጸሎት ቤት፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ ሰንበት፣ መጋቢት 23፣ 2015 ከኢንዶኔዥያ በስተምስራቅ እና በሰሜን አውስትራሊያ የምትገኘው ፓፑዋ ኒው ጊኒ (ፒኤንጂ) ብዙ ጊዜ ከአለም የመጨረሻ ድንበሮች አንዱ፣ የመጨረሻው ገነት ተብሎ ይጠራል። በተጨማሪም ብዙውን ጊዜ ያልተጠበቀው መሬት ተብሎም ይጠራል። ፒኤንጂ ውብ ሀገር ናት - በተፈጥሮ ሃብት የበለፀገች፣ ሚሲዮናውያን፣ የህክምና ባለሙያዎችና ማዕድን ቆፋሪዎች የሚሄዱበት ቦታ ነዉ፤ ነገር ግን ቱሪስቶች እምብዛም አይጎበኙትምL። ታላቅ የባህልና የቋንቋ ብዝሃነት ያለው ታዳጊ ሀገር እንደመሆኑ፣ PNG ከ800 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች አሉት። የሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ተሐድሶ እንቅስቃሴ የተቋቋመው በ1998 ሲሆን የምሥራቹ በሰሜናዊና ደጋማ የአገሪቱ ግዛቶች ወደ ብዙ አዳዲስ አካባቢዎች በመስፋፋቱ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ቀደም ባሉት ጊዜያት ጥንቆላና አረመኔያዊ ድርጊቶች በነበሩባቸው አካባቢዎች አሁን አብያተ ክርስቲያናትና ቡድኖች ተፈጥረዋል። በደቡብ የሀገሪቱ ክፍል የሚደረገውን ሥራ ለመድረስና ለመመስረት ለተወሰኑ ዓመታት በወንድሞቻችን ልብ ውስጥ ሀሳብ ነበራቸዉ። የፒኤንጂ ዋና ከተማ የሆነችው ፖርት ሞርስቢ በስተደቡብ የምትገኝ ሲሆን በተራራማ መሬት አቀማመጥና ጥሩ መንገድ ባለመኖሩ ምክንያት በዋነኛነት በአየር ወይም በባህር ትራንስፖርት መጠቀም ያስፈልጋል። እ.ኤ.አ. በ2019 አንድ ሚኒስተር ከፒኤንጂ ወደ ሰሜን ፖርት ሞርስቢ አካባቢ ተዘዋውሯል፤ በዚህም ፍላጎቶችን ለመከታተልና በዋና ከተማው ዙሪያ ሥራውን ለማቋቋም አዲስ ተልዕኮ ተጀመረ። በበርካታ የዓለም ግምገማዎች መሠረት፣ ፖርት ሞርስቢ በዓለም ላይ ለመኖር እጅግ አመቺ ካልሆኑ ወይም ከማይመረጡ ከተሞች መካከል አንዱ ነው። በዚህ ከተማ ስርቆት፣ እገታና ብጥብጥ በጣም የተለመደ ነው እናም ወንድሞቻችን የእግዚአብሄርን ስራ በሚሰሩበት ጊዜ ይህ ያጋጥማቸዋል፣ እያጋጠማቸዉም ነው። ስራው በተሳካ ሁኔታ ወደፊት እንዲሄድ፣ በዚህ የወይኑ ቦታ ላይ ለጌታ የብርሃን ማማ ለመስራት በአስተማማኝ ቦታ የሚገኝ መሬት ወይም ንብረት በጣም ያስፈልጋል። የእግዚአብሔር ምሕረት ታላቅ እንደሆነና በዚህች ምድር ታሪክ መገባደጃ ሰአታት ውስጥ፣ እንደ ነነዌ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እንኳን የሚደረሱ ብዙ ነፍሳት እንዳሉ እንገነዘባለን። ስለዚህ በዚህ ስራ ከእኛ ጋር እንድትተባበሩና በልግስና እንድትሰጡን በዚህም ይህ የብርሃን ማማ እንዲቋቋም እና ስራው ወደፊት እንዲቀጥል እንጠይቃለን። ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፥ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።" (ኢሳ 42፡12)። እግዚአብሔር አብዝቶ እንዲባርካችሁ እንጸልያለን! ወንድሞችና እህቶች ከፓፑዋ ኒው ጊኒ ደቡብ ሚሽን
 <<    >>