Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሰኔ 17፣ 2015 13ኛ ትምህርት
የሰንበት ቀን ደስታዎች የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፥ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም። ሰባራውን ጠጋኝ፥ የመኖሪያ መንገድን አዳሽ ትባላለህ። (ት. ኢሳያስ 58:12)
ለንባብ የተመረጠዉ፡   Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 349–368. 
የሰን በትን ትክክለኛ አከባበር በተመለከተ አገልጋዮች በጥንቃቄ መመሪያ መስጠት አለባቸው። በእሁድ ቀን ጠባቂዎች ዘንድ ያለው የላላ አሠራር የእግዚአብሔርን ቅዱስ የዕረፍት ቀን እናከብራለን የሚሉሰዎች እንዳይከተሉ ልንጠነቀቅ ይገባል። የድንበሩ መስመር የእግዚአብሔርን መንግሥት ምልክት በተሸከሙት እና የአመፃ መንግሥት ምልክት በተሸከሙት መካከል ግልጽ የሚታይ እና የተለየ መሆን አለበት።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 353.

1. ስድስት ቀናት እሁድ ሰኔ 11
ሀ. የሳምንቱ ስድስቱ ቀናት የተሰጡን ወይም የታቀዱት ምን እንድናደርግ ነው—ይህስ በክርስቲያን ሕይወት ውስ ጥ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ዘጸአት 20:9; 2ኛ ተሰሎንቄ 3:10 ለ. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ውን ቀን አብራራ - እና በእነዚያ ስድስት ቀናት ውስጥ ምን ማስታወስ እንዳለብን ጭምር፡፡ ዘፍጥረት 1:5; ዘሌዋውያን 23:32; ዘጸአት 20፡8 ሳምንቱን በሙሉ ሰንበትን በልባችን ልናስብና በትእዛዙ መሰረት ለማክበር መዘጋጀት አለብን ። ሰንበትን እንደ ህጋዊ ጉዳይ ማክበር ብቻ አይደለም። ከሁሉም የሕይወት ሁኔታዎች ጋር ያለውን መንፈሳዊ ግንኙነቱን መረዳት አለብን።” —Testimonies for the Church, vol. 6, p. 353.ሰንበት እንደዚህ በሚታሰብበት ጊዜ፣ ጊዜያዊው ነገር መንፈሳዊ ውን ነገር እንዲነካብን አንፈቀድለትም። በስድስቱ የስራ ቀናት ዉስጥ መሠራት ያለበት ምንም አይነት ግዴታ ተርፎ ለሰንበት ቀን ማደር የለበትም። ጌታ ባረፈበት ቀን በአገልግሎቱ ለመካፈል በጣም እንዳንደክም በሳምንቱ ዉስጥ ኃይላችን ለጊዜያዊ ነገሮች በመሮጥ ማድከም የለብንም።”—Ibid., p. 354.

2. ትክክል ሰንበትን እንድንጠብቅ የሚረዱ ቁልፍ ነገሮች ሰኞ ሰኔ 12
ሀ. ከሰንበት በፊት ያለው ስም ማን ይባላል እና በዚያ ቀን ምን መደረግ አለበት? ማርቆስ 15:42; ዘጸአት 16:22, 23 በትእዛዙ መሠረት ሰንበትን ለማክበር በእውነት የሚጨነቁ ሁሉ በሰንበት ምንም ምግብ አያበስሉም። ሕጉን በሲና የሰጠውን እግዚአብሔርን በመፍራት ራሳቸውን ክደው በስድ ስተኛው ቀን የተዘጋጀውን ምግብ ይበላሉ፣ ምንም እንኳን ደስ የ ማይል ቢሆንም። እግዚአብሔር የእስራኤል ልጆች በሰንበት ቀን መጋገርና ማብሰል ከልክሏቸው ነበር።”—The Spirit of Proph-ecy, vol. 1, p. 225.በሰንበት ምግብ ማብሰል መወገድ አለበት፤ ነገር ግን ስለዚህ ቀዝቃዛ ምግብ መመገብአስፈላጊ አይደለም። በቀዝቃዛው የአየር ጠባይ ወቅት ከአንድ ቀን በፊት የተዘጋጀውን ምግብ ማሞቅ አስፈላጊ ነዉ።”—The Ministry of Healing, p. 307.“ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ዓለማዊ ሥራዎች ሁሉ ተሠርተዉ ይለቁ ወይም ይወገዱ፤ እንዲሁም ሁሉም ዓለማዊ ወረቀቶች ከዓይኖቻችን ፊት ይወገዱ።”—Testimonies for the Church, vol. 6, p. 355. ለ. በዚያ ቀን አንዳንድ ነገሮች ባይጠናቀቁም መንፈሳዊ ዝግጅት ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ሉቃስ 23:54–24:1; ማቴዎስ 5:23, 24 ብዙዎች በግዴለሽነት ጫማቸውን ቀለም መቀባትና መላጨትን፣ እስከ ሰንበት መጀመሪያ ድረስ አያደርጉትም። ይህ መሆን የለበትም። በሥራ ቀን እንዲህ ዓይነትቱን ሥራ መሥራትን ቸል ቢሉ ፣ ሰንበት እስኪሸኝ ድረስ ጢማቸውን ሳይላጩ፣ ጫማቸውን ሸካራና ያለተቀባ እንዲሆን በመተዉ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ጊዜ በቂ አክብሮት ሊሰጡ ይገባል። ይህም የማስታወስ ችሎታቸውን ሊረዳቸው እና በስድስቱ የሥራ ቀናት ውስ ጥ የራሳቸውን ሥራ ሳይረሱ እንዲሠሩ ለሌላ ጊዜ የበለጠ እንዲጠነቀቁ ያደርጋቸዋልና።”—The Signs of the Times, May 25, 1882.በዚህ ቀን በወንድማማቾች መካከል፣ በቤተሰብም ሆነ በቤተክርስቲያን፣ ያሉ ልዩነቶች ሁሉ መወገድ አለባቸው። ምሬትና ቁጣ ክፋትም ሁሉ ከነፍስ ይውጡ። በትሕትና መንፈስ “እርስ በርሳችሁ በደላችሁን ተናዘዙ፣ ትፈወሱም ዘንድ እርስ በርሳችሁ ጸልዩ ። ያእቆብ 5:16።——Testimonies for the Church, vol. 6, p. 356. ሐ. ለሰንበት እና ለአምልኮ ቦታዎች ለመዘጋጀት ንጽህና ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ዘጸአት 19:10, 11; 30፡18–20። ሁሉም በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሲካፈሉ የሚለብሱት ልዩ የሰንበት ልብስ ሊኖራቸው ይገባል። ከዓለማዊ ፋሽን ጋር መስማማት ባይገባንም ውጫዊ ገጽታችንን በተመለከተ ደንታ ቢስ መሆን የለብንም። ምንም ጌጥ ሳናደርግ ንጹሕና የተስተካከልን (ፀጉራችን የተከረከምን) መሆን አለብን። የእግዚአብሔር ልጆች ከውስጥም ከውጪም ንጹሕ መሆን አለባቸው።”—Ibid., p. 355.

3. የራሳችን (የግል) ሥራ ማክሰኞ ሰኔ 13
ሀ. ሰንበትን በሚመለከቱ የተሰጡ የአምላክ ትእዛዛት ምን ያህል ጥብቅ እንደሆኑ የሚያሳየው ምንድን ነው? ዘጸአት 31:14; ነህምያ 13፡15–18 ለ . ሸክሞችን ስለመሸከምና ስለአላስፈላጊ ጉዞስ? ኤርምያስ 17:21, 22ለታዛዦች የተገባዉን የተስፋውን ቃል ከፈለግን ሰንበትን አጥብቀን ማክበር አለብን። ሊወገድ ወይም ሊቀር የሚችለዉን አላስፈላጊ ጉዞ በዚህ ቀን ብዙ ጊዜ እንጓዛለን ብዬ እፈራለሁ። የሰንበትን አከባበር በተመለከተ ጌታ ከሰጠው ብር ሃን ጋር በመስማማት በዚህ ቀን በጀልባዎች ወይም በመኪናዎች ላይ ስለመጓዝ የበለጠ መጠንቀቅ አለብን። በእነዚህ ጉ ዳዮች ከልጆ ቻችን እና ከወጣቶቻችን ፊት ትክክለኛ አርአያ መሆን አለብን። የእኛን እርዳታ ወደሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት ለመድረስ እና እግዚአብሔር እንዲሰሙት የሚፈልገውን መልእክት ለእነርሱ ለመስጠት በሰንበት መጓዙ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በተቻለ መጠን ቲኬቶቻችንን ሆነ ሌሎች ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶችን በሌላ ቀን ማድረግ አለብን። ጉዞ ስንጀምር በሰንበት ቀን ወደ መድ ረሻችን እንዳንደርስ ለማቀድ የተቻለንን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለብን።በሰንበት ለመጓዝ ስንገደድ ትኩረታችንን ወደ ዓለማዊ ነገሮች ከሚስቡ ሰዎች ጋር ላለመገናኘት መሞከር አለብን። አእምሯችንን በእግ ዚአብሔር ላይ ማኖርና ከእርሱ ጋር መነጋገር አለብን ። በማንኛውም አጋጣሚ እውነትን በተመለከተ ለሌሎች መናገር አለብን። መከራን ለማስታገስና የተቸገሩትን ለመርዳት ምን ጊዜም ዝግጁ መሆን አለብን። እንደዚህ ባሉ አጋጣሚዎች እግዚአብሔር የሰጠን እውቀትና ጥበብ እንድንጠቀምበት ይፈልጋ ል። ነገር ግን ስለንግድ ነክ ጉዳዮች ማውራት ወይም በማንኛ ውም የተለመደና ዓለማዊ ውይይት ውስጥ መካፈል የለብንም። በማንኛውም ጊዜና በሁሉምቦታ እግዚአብሔር ሰንበትን በማክበር ለእርሱ ታማኝ መሆናችንን እንድናሳይ ይፈልገናል።”—Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 359, 360. ሐ. ንግግራችንና ሀሳባችንስ? ኢሳይያስ 58:13 እግዚአብሔር የሚፈልገው በሰንበት ከሥጋዊ ሥራ እንድንርቅ ብቻ ሳይሆን፣ አእምሮም በቅዱሳን ጉዳዮች ላይ እንዲ ያተኩር እንዲሰለጥን ነው። አራተኛው ትእዛዝ በዓለማዊ ነገሮች ላይ በመነጋገር ወይም በተራና ቀላል በሆነ ውይይት በመሳተፍ ልንተላለፈዉ እንችላለን። ወደ አእምሮ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር ወይም ሁሉንም ነገር ማውራት የራሳችንን ቃላት (ሀሳብ) መናገር ነው። ማንኛውም ከእዉነት ማፈንገጥ ለኃጢአት ባርነትና ለኩነኔ ያደርገናል።—Ibid., vol. 2, p. 703.

4. መሐሪዉ ፈጣሪያችን ረቡዕ ሰኔ 14
ሀ. በሰንበት ቀን አምልኮ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? ከአምልኮ ጋር ምን ይያያዛል? ዘሌዋውያን 23:3; የሐዋርያት ሥራ 15:21; ሉቃስ 4፡16 ለ. በተለይ አሁን በምን ጉዳይ መሳተፍ አለብን—ለምንስ? ዕብራውያን 10:24, 25 “የቅዱሳንን ሕብረት (መሰብሰብ) አስፈላጊነት የማይሰማቸው፣ ጌታ ከእነሱ ጋር እንደሚገናኝ ባለው ውድ ማረጋገጫ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገውን እርዳታ ምን ያህል አቅልለው እንደሚመለከቱት ያሳያሉ ።”—The SDA Bible Commentary [E. G. White Comments], vol. 7, p. 934. ሐ. በሥቃይ ላይ ላሉ ሰዎች እርዳታ መስጠት እንደ ሥራ ይቆጠራል ወይስ ከአምልኮ ጋር የሚስማማ ነው? ማቴዎስ 12፡10-13 ሁሌም ቢሆን የሚሰቃየውን የሰው ልጅ ስቃዩን ለማስታገስ በሰንበት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ይኖራሉ። “ምሕረትን አደርጋለሁ፤ መሥዋዕትም አይደለም” ባለው በእርሱ ሕግ መሠረት ይህ ትክክል ነው። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ በግዴለሽነት ውስጥ የመውደ ቅና በሰንበት ቀን ማድረግ አስፈላጊ ያልሆነውን ነገር የማድረግ አደጋ አለ።”—Medical Ministry, p. 50. መ. የሱስ በሰንበት ለመፈወስ የመረ ጠው ለምንድን ነው? ዮሐንስ 5:5-9 [የሱስ]ሰንበትን ከበረከት ይልቅ መርገም እንድትሆን ካደረት ቀንበር ለማላቀቅ ነበር የሱስ የመጣው።በዚህ ምክንያት ነበር በቤተሳይዳ የፈወስ ተግባሩን ለማካሔድ የሰንበትን ቀን የመረጠው። ድውዩን ሰው ከሣምንቱ በማንኛውም ቀን ሊፈውሰው ወይም አልጋህን ተሸክመህ ሒድ ሳይል እንዲሁ ሊያድነው ይችል ነበር። ይህን ቢያደርግ ኖሮ የተመኘውን ጥሩ አጋጣሚ አያስገኝለትም ነበር። የሱስ በምድራዊ ሕይወቱ ባከናወነው ተግባር ሁሉ በጥበብ የተቀየሰ ዓላማ ነበረው። እርሱ የሠራው እያንዳንዱ ድርጊት በራሱም ሆነ በትምህርት ሰጭነቱ ዋና ነበር። የመፈወስ ኃይሉን ለመጠቀም በኩሬው ከነበሩት ሕሙማን መካከል የባሰበትን መርጦ በመፈወስና በእርሱ ላይ የተፈጸመውን ታላቅ ድርጊት ለማሳወቅ አልጋውን ተሸክሞ በከተማው መካከል እንዲያልፍ አዘዘው። ይህም በሰንበት ቀን መደረግ ስለሚገባው ነገር ጥያቄ በመቀስቀስ አይሁዶች ስለ ጌታ ቀን የደነገጉትን ለማውገዝና ባሕላቸውን ከንቱ ለማድረግ በር ከፈተለት። —የዘመናት ምኞት፣ ገጽ 206 (194)

5. ትምህርት ከተፈጥሮ ሐሙስ ሰኔ 15
ሀ. ስለ ሰንበት አጠባበቅ ሌላ አስፈላጊ ገጽታ አብራራ። ዘጸአት 20:11; ሮሜ1:20; የሐዋርያት ሥራ 16፡13 የሰንበት ትምህርትና የአምልኮ ስብሰባ የሰንበትን የተወሰነ ክፍል ብቻ ይይዛሉ። ለቤተሰቡ የሚቀረው ክፍል ከሁሉም የሰንበት ሰዓቶች ሁሉ እጅግ የተቀደሰ እና ውድ ወቅት ሊሆን ይችላል። አብዛ ኛውን ጊዜ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ማሳለፍ አለባቸው። በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ ትንንሽ ልጆች በተቻለ መጠን መዝናኛን ለማግኘት ለራሳቸው ይተዋሉ። ብቻቸውን ሲቀሩ ልጆቹ ብዙም ሳይቆይ እረፍት ያጡና መጫወት ይጀምራሉ ወይም የሆነ ዓይነት ጥፋት ውስጥ ይገባሉ ። ስለዚህ ሰንበት ለእነርሱ ምንም የተቀደሰ ትርጉም አይኖራቸዉም።በአስደሳች የአየር ሁኔታ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በየሜዳውና በጫካ ውስጥ ይራመዱ። በተፈጥሮ ውብ ነገሮች መካከል የሰንበትን ተቋም ምክንያት ይንገሯቸው። የእግዚአብሔርን ታላቅ የፍጥረት ሥራ ይግለጹላቸው። ምድር በእጁ በተሰራች ጊዜ የተቀደሰች እና የተዋበች እንደነበረች ይንገሯቸው። አበባ ሁሉ ፣ ቁጥቋጦው፣ ዛፍ ሁሉ ለፈጣሪያቸዉ ምላሽ እንደሚሰጡ ይንገሯቸዉ። ዓይን ያረፈበት ነገር ሁሉ የሚወደድና አእምሮን በእግዚአብሔር ፍቅር ሀሳቦች የሚሞላ እንደነበረ፤ እንዲሁም ሁሉም ድምፅ ከእግዚአብሔር ድምፅ ጋር የሚስማማ ሙዚቃዊ ቃና ያለዉ እንደነበረ ያስረዷቸዉ። የእግዚአብሔርን ፍጹም ሥራ ያበላሸው ኃጢአት መሆኑን፤ እሾህና አሜከላ፣ ኀዘን፣ ሕመም፣ ሞትም ሁሉ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ምክንያት የመጡ መሆነቸዉን ያሳዩዋቸዉ። ምንም እንኳ ምድር በኃጢአት እርግማን ምክንያት ብትፈራርስም፤ አሁንም የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዴት እንደምትገልጥ ይንገሯቸው። . . .የመዳንን መንገድ ንገሯቸዉ። . . . የቤተሌሔሙ ጣፋጩን ታሪክ ደጋግመዉ ይንገሯቸዉ። የሱስ፣ በልጅነቱ ለወላጆቹ ታዛዥ፣ እንደ ወጣት ደግሞ ታማኝና ታታሪ፣ ቤተሰቡን የሚደገፍና የሚረዳ እንደነበረ ያስረዷቸዉ። ስለዚህ አዳኛችን ወጣቶች ላይ የሚደርሱትን ፈተናዎችን ፣ እንቆቅልሾችንና መከራዎችን፣ እንዲሁም የወጣቶችን ተስፋና ደስታ ስለሚያውቅ እንደሚራራላቸውና እንሚረዳቸው ልታስተምራቸው ትችላላችሁና።”—Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 358, 359

የግል ግምገማ ጥያቄዎች አርብ ሰኔ 16
1. በሳምንቱ ውስጥ ከመጠን በላይ መሥራት እንዴት የሰንበትን እረፍት እየተጋፋብኝ ሊሆን ይችላል? 2. ምንም እንኳን ባይጠናቀቅም አርብ ጀንበር ስትጠልቅ ሁሉንም ስራዎች ማቆም ያለብን ለምንድን ነው? 3. ሰንበትን በተመለከተ የጉዞ ልማዶቼን እንዴት ማሻሻል እችላለሁ? 4. በሰንበት ማክበር እና የ ታመሙትን በመርዳት ሚዛኑን ግለጽ። 5. እኛ እንደ ወላጆች ልጆቻችን ሰንበትን እንዲያደንቁ ለመርዳት ምን ማድረግ እንችላለን?
 <<    >>