Back to top

Sabbath Bible Lessons

ደማቅ የብርሃን ጨረሮች - የእውነት ውድ ቅርሶች (2)

 <<    >> 
ሰንበት፣ ሚያዝያ 21፣ 2015 5ኛ ትምህርት
የሺህ አመታት የምድር ባዶ መሆን (I) መታሰቢያ ጥቅስ ፡- የቀሩቱ ሙታን ግን ይህ ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በሕይወት አልኖሩም። ይህ የፊተኛው ትንሣኤ ነው። በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፥ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።” (ራእይ 20:5, 6)
ለንባብ የተመረጠዉ፡   The Great Controversy, pp. 653–661. 
ያላገጡባቸውንና የተሳለቁባቸውን፣ ፈጽመው ያጠፏቸውም ዘንድ የፈለጓቸውን እነዚያውን መደቦች በቸነፈር፣ በማዕበልና በመሬት መናወጥ ውስጥ ምንም ሳይሆኑ ሲያልፉ ዓለም አየ። ለሕጉ ተላላፊዎች እንደሚፋጅ እሳት የሆነው እርሱ ለሕዝቦቹ ከአደጋ መጠለያ እልፍኝ ነው።”— The Great Controversy, pp. 654.

1. የሺህ አመታትን መጀመር እሁድ ሚያዝያ 15
ሀ. በሺህ ዓመት (በሚሊኒየሙ) መጀመሪያ ላይ ምን ክስተት ይከናወናል? ራእይ 20:5 ለ. በመጀመሪያው ትንሣኤ የሚነሳው ማን ነው? ይህ የሚሆነው መቼ ነው? ራእይ 20:6 (የመጀመሪያ አጋማሽ)፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15:22, 23 የትንሣኤ እውነታ እያንዳንዳችን በጸሎት እንድንመረምር ሊያነሳሳን የሚገባን ነገር ምንድን ነው? ክርስቶስ በክብሩ ተገልጦ ጻድቃን ሙታንን ይጠራል። ሕያዋን ቅዱሳን ይለወጣሉ፣ እናም ከሞት ከተነሡት ሙታን ጋር፣ ጌታቸውን በአየር ላይ ለመገናኘት በመላእክት ከምድር ከፍ ብሎ ይነሳሉ። ምድር እንደ ምድረበዳ ሆና ትቀራለች።”—Spiritual Gifts, vol. 3, p. 83.ሰዎች በየሱስ ታላቅ እምነት እንዳላቸው እና ምንም ልታደርጉት የምትችሉት ነገር እንደሌለ ክርስቶስ እንደሚያደርግላችሁ ይናገሩ ይሆናል። አሁን፣ ክርስቶስ ሙታንን በሚጠራበት ጊዜ፣ ለዘለአለም ህይወት ትንሳኤ ወይም ትንሳኤ ለፍርድ የሚሆንበት ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በእርስዎ ተግባር ላይ የሚወሰን ነው።”— Faith and Works, p. 55.

2. የጻድቃን ትንሣኤ ሰኞ ሚያዝያ 16
ሀ. ጻድቃን በሺህ ዓመቱ መጀመሪያ ላይ በክርስቶስ መምጣት ትንሣኤ ሲያገኙ የሚታወቁት የትኞቹ ልዩነቶች ናቸው? ራእይ 20:4-6 ክር ስቶስ . . . የዳግም ምጽአቱን ጊዜ በጉጉት ይጠባበቃል። ያን ጊዜ ጻድቃን ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፣ ሕያዋንም ቅዱሳን ሞትን ሳያዩ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይወሰዳሉ።”—የዘመናት ምኞት፣ ገጽ. 530.ሕይወት ሰጪው የተገዛውን ንብረቱን በመጀመሪያው ትንሣኤ ይጠራል፣ እናም እስከዚያች የድል ሰዓት ድረስ፣ የመጨረሻው መለከት ሲነፋና ሰፊው ሰራዊ ት ወደ ዘላለማዊ ድል እስከሚወጣ ድረስ፣ የተኛ ቅዱሳን ሁሉ በደህና ልክ በእግዚአብሔር ስም እንደሚታወቅ ውድ ዕንቁ ይጠበቃል። በሕይወት እያሉ በእነርሱ ባደረባቸው በአዳኙ ኃይል የመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች ስለነበሩ፣ አሁን ከሞት ተነስተዋል።“ሰዓትቱ እየመጣች ነው” ሲል ክር ስቶስ ተና ግሯል፡- “በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበትና የሚወጡበት ጊዜ ነው። ያ ድምፅ በሙታን መኖሪያ ሁሉ ውስ ጥ ይሰማል፤ በየሱስም ስም የተኙት ቅዱሳን ሁሉ ነቅቶ ከእስር ቤታቸዉ ይወጣሉ። ያኔ ከክር ስቶስ ጽድቅ የተቀበልነው የምግባር በጎነት ከፍ ወዳለ የሥርዓት ታላቅነት ጋር ያደርሰናል።”—Sons and Daughters of God, p. 359ለመጀመሪያው ትንሣኤ የሚበቁት ብፁዕና ቅዱሳን ብቻ ናቸው። ክርስቶስ ሲመጣ ባህሪውን አይለውጥምና ። . . . ያለ ነቀፋ፣ ያለ ነቁጣ ወይም ያለ መጨማደድ ወይም ያለምንም ግድፈት እንድንገኝ የእግዚአብሔር ቃል አስረግጦ ይነግረናል። አሁን መታዘዝን፣ እግዚአብሔር በእኛ እንዲሰራና እኛም እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነገርን እንድንሠራ እንዲሁም ለገዛ መዳናችን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መሥራት እንድንችል ራሳችን ለመለኮታዊዉ ፈቃድ አሳልፎ መስጠትን መማር አለብን። ነገር ግን የራሳችን ጥረት ብቻዉን የኃጥአት ይቅርታን ለማስገኘትም ሆነ ልብን ለመለወጥ ምንም አቅም የለዉም። ለእኛ ስርየት የሚያስገኝልን የክርስቶስ ደም ብቻ ነው፤ በውስጣችን ንጹህ ልብ የሚፈጥርልንና የእግዚአብሄርንም ህግ እንድንታዘዝ የሚያስችለን የእርሱ ፀጋ ብቻ ነው፡፡ ተስፋችን የተማከለው በእርሱ ብቻ ነው”—The Signs of the Times, February 9, 1891. ለ. ክርስቶስ ለሚወዱት የሚመለስበትን መንገድ ገምግም። 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡13–16። ክርስቶስ ሁሉንም በስሙ ያመኑትን የእርሱ እንደሆኑ ገልጿል። በሟች ሥጋ ውስጥ የሚኖረው የክርስቶስ መንፈስ ሕያው ኃይል የአማኙን ነፍስ ከየሱስ ክርስቶስ ጋር ያስራል። በየሱስ የሚያምኑት በእርሱ ልብ የተቀደሱ ናቸው፤ ሕይወታቸው ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ተሰውሮአልና። ”— Selected Messages, bk. 2, p. 271.

3. የሰማዩ ቤት ማክሰኞ ሚያዝያ 17
ሀ. ሕያዋን ጻድቃን ከሞት ከተነሱት ቅዱሳን ጋር ምን ይሆናሉ? 1ኛ ተሰሎንቄ 4:17 [ክርስቶስ] እግዚአብሔርን ሰድቧል በሚል ተከሰሰ፣ በጭካኔ ሞት ተፈረደበት፣ ነገር ግን የመቃብሩን እስራት በጣጠሰ፣ ከሙታንም በድል ተነሳ፣ እና በተቀበረው የዮሴፍ መቃብር ላይ ሆኖ፡- እኔ ትንሳኤ ነኝ። ሕይወትም።” (ዮሐንስ 11፡25) በሰማይና በምድ ር ያለው ኃይል ሁሉ ለእርሱ ተሰጥቷል፣ ጻድቃንምደግሞ ከመቃብር በየሱስ ነጻ ይወጣሉ ። ያን ዓለምና ከሙታን ትንሣኤ ለማግኘት ብቁ ሆነው ይቆጠራሉ። …የትንሳኤ ጧት እንዴት ያለ የከበረ ጠዋት ይሆናል! ክርስቶስ በሚያምኑት ለመደነቅ ሲመጣ እንዴት ያለ አስደናቂ ትዕይንት ይከፈታል! ከክርስቶስ ጋር በውርደቱ እና በመከራው ተካፋዮች የነበሩት ሁሉ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች ይሆናሉ። ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ በየሱስ ያንቀላፉ አማኝ ቅዱሳን ሁሉ ከዚያ እስር ቤታቸዉ በድል አድራጊነት ይወጣሉ። …የሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የመቃብርን እስራት በጠሰ፣ እናም በመቃብር ውስጥ የሚያንቀላፉ ሁሉ ድሉን ይካፈላሉ። ድል አድራጊው እንዳደረገው ከመቃብራቸውም ይወጣሉ።”—Selected Messages, bk. 2, pp. 271, 272 ለ. እንዴት አንድ ላይ ይሰበሰባሉ እንዲሁም ለምን ዓላማ? ማቴዎስ 24:29–31ዮሐንስ 14:3፤ 13፡36። የአዳኛችንን መምጣት ለረጅም ጊዜ ጠብቀናል። ሆኖም ግን የተስፋው ቃል የታመነ ነው። በቅርቡ በተስፋው ቤታችን እንሆናለን። በዚያ የሱስ ከእግዚአብሔር ዙፋን በሚፈሰው ህያው ጅረት አጠገብ ይመራናል እናም ባህሪያችንን ፍፁም ለማድረግ ከዓለም ጨለማ አንዳመጣን ያስረዳናል። እዚያም ወደነበሩበት የተመለሱትን የዔድንን ውበቶችን በማይደበዝዝ ዕይታ እናያለን። በራሶቻችን ላይ ያደረግልንን አክሊል በቤዛችን እግር ስር አስቀምጠን የወርቅ በገናዎቻችንን እየደረደርን በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰማያትን ሁሉ በምስጋና እንሞላዋለን።”—Testimonies for the Church, vol. 8, p. 254.እግዚአብሄር ይመስገን! ስፈልጋቸዉ የነበሩት እነዚህ መኖሪያ ቤቶች ናቸው። በኃይለኛው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሚጠፉ እንደ ምድራዊ መኖሪያ ቤቶች አይደሉም። ነገር ግን ክርስቶስ በእርሱ ለሚያምኑት ለማዘጋጀት የሄደው እነዚያ ሰማያዊ መኖሪያ ቤቶች ናቸው። በዚህ ምድር ላይ ምንም ቤት የለንም። እኛ እዚህ ወደ ተሻለ ሀገር፣ ወደ ሰማያዊም የምንጓዝ የሃይማኖት ተጓዦችና እንግዶች ብቻ ነን።”—In Heavenly Places, p. 354.

4. የክፉዎች ዕጣ ረቡዕ ሚያዝያ 18
ሀ. በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ወቅት ክፉዎች ምን ይደርስባቸዋል—ለምንስ? 2ኛ ተሰሎንቄ 1:7, 8; 2፡7፣8። ኃጥአን፣ እግዚአብሔርን ወይም ባልንጀሮቻቸውን ቸል በማለታቸው ሳይሆን እግዚአብሔር ስላሸነፈ በፀፀት ተሞሉ። ውጤቱ አሁን የሚታየው ስለሆነ ሙሾ አወረዱ፤ ከኃጢአታቸው ግን ንስሐ አልገቡም። ቢቻላቸውስ ድል ለመንሳት የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 654ከዚህ ላይ ክርስቶስ ሰዎች ለዘላለም የሚዘጋጁበት አንድ ሺ ዓመት መናገሩ አይደለም። ሊነግረን የፈለገዉ አብይ ነገር በኖኅ ዘመን እንደነበረዉ እንዲሁም በሰዉ ልጅ መምጫ ጊዜ እንደሚሆን ነዉ። —The Desire of Ages, p. 633. ለ. ይህን በቀል ግለጽ። ራእይ 19:11-16ኢሳይያስ 24:17–22ኤርምያስ 25:30-33 አሁን ሁሉም ውሳኔአቸውን አድርገዋል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ከሚያደርገው ጦርነት ኃጥአን ሙሉ ለሙሉ ከሰይጣን ጋር አብረዋል። የተረገጠው ሕጉ ስልጣን ትክክል እንደሆነ እግዚአብሔር የሚያሳይበት ሰዓት መጥቶአል። አሁን ተቃርኖው ከሰይጣን ጋር ብቻ አይደለም፤… ከሰዎችም ጋር እንጂ። “እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና”፤ “ኃጥአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል። . . .የውድመት ሥራ፣ የሕዝቡ መንፈሳዊ ጠባቆች እንደሆኑ በመሰከሩት መካከል ተጀመረ፤ ሐሰተኛ ዘቦች መጀመሪያ ወዳቂዎች ሆኑ። ሊታዘንላቸው ወይም ሊተርፉ የሚችሉ አንዳች የሉም። ወንዶች፣ ሴቶች፣ ልጃገረዶችና ትናንሽ ልጆች አንድ ላይ ጠፉ።”— ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 656 ሐ. እነዚህ ሁሉ ሙታን ምን እንደሚሆኑና በዚያን ጊዜ የምድርን ሁኔታ ግለጽ። ራእይ 19:17–21ኤርምያስ 4:23-29ኢሳይያስ 24:1-4 ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ኃጥአን ከምድረ ገጽ ይጠፋሉ፦ ከአፉ በሚወጣው መንፈስ ይበላሉ፤ በክብሩም ነፀብራቅ ይጠፋሉ። ክርስቶስ ሕዝቦቹን ወደ እግዚአብሔር ከተማ ይወስዳቸዋል፤ ምድርም ነዋሪ-አልባ ትደረጋለች። . . .መላዋ ምድር ምንም የሌለባት ምድረ በዳ መሰለች። በመሬት መንቀጥቀጥ የወደሙት ከተሞችና መንደሮች፣ የተፈነገሉት ዛፎች፣ በባህር የተወረወሩት ወይም በምድር በራስዋ የተተፉት የተሰነጣጠቁ ቋጥኞች፣ በምድር ላይ ተበትነዋል፤ ከምድር በታች ያሉ ዋሻዎችም ከመሰረታቸው የተቀደዱት ተራሮች የት እንደነበሩ ምልክት ሆኑ።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 657

5. ባዶነት ሐሙስ ሚያዝያ 19
ሀ. በዚህ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ከቅዱስ አምላክ እንዲህ ያለውን ቁጣ ለማግኘት ምን ሲያደርጉ ቆይተዋል? ኢሳይያስ 24:5, 6 ለስድስት ሺህ ዓመታት ታላቁ ተጋድሎ (ተቃርኖ) ሲካሄድ ኖሮአል። የሰውን ልጆች ያስጠነቅቁ፣ እውቀት እንዲኖራቸውና እንዲድኑ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅና ሰማያዊ መልዕክተኞች ከክፉው ኃይል ጋር ሲፋለሙ ቆይተዋል። አሁን ሁሉም ውሳኔአቸውን አድርገዋል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ከሚያደርገው ጦርነት ኃጥአን ሙሉ ለሙሉ ከሰይጣን ጋር አብረዋል። የተረገጠው ሕጉ ስልጣን ትክክል እንደሆነ እግዚአብሔር የሚያሳይበት ሰዓት መጥቶአል። አሁን ተቃርኖው ከሰይጣን ጋር ብቻ አይደለም፤… ከሰዎችም ጋር እንጂ። “እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና”፤ “ኃጥአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 656. ለ. ይህ ፍጻሜው ነው? ኤርምያስ 4:27 በዚህ ሁኔታ ውስጥ ለምን ያህል ጊዜ ይቆያሉ? ራእይ 20:5 ኃጥአን ጠፍተው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ሙት አካላቸው በምድር ላይ ተዘርሮ ይታይ ነበር። የመጨረሻዎቹን መቅሰፍቶች የያዘው የእግዚአብሔር ቁጣ የምድር ነዋሪዎችን በመጎብኘቱ ኃጥአን ከህመም የተነሳ ጥርሶቻቸውን እንዲያፋጩና እግዚአብሔርን እንዲራገሙ አድርጎአቸው ነበር። ለያህዌ ቁጣ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች የነበሩት ሐሰተኛ እረኞች ዐይኖቻቸው ወደ ውስጥ ሰርጉደውና ምላሳቸው በላንቃቸው ላይ ተጣብቆ ነበር፡፡ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ድምፅ ከዳኑ በኋላ ኃጥአን እርስ በርስ በቀላቸውን ይወጡ ጀመር። ምድር በደም ጎርፍ የተሞላች መሰለች። ሙት አካል ከአንደኛው የምድር ጫፍ እስከ ሌላኛው ደረሰ።”—ቀደምት ጽሑፎች ገጽ 289, 290ስለ ሰይጣን መወገድ፣ ምድርም ወደምትገባበት የምስቅልቅልና የውድመት ሁኔታ ገላጩ [የሱስ] አስቀድሞ ይናገራል። ይህ ሁኔታም ለአንድ ሺህ አመት እንደሚቆይ ይናገራል።”—ታላቁ ተጋድሎ፣ ገጽ 658.

የግ ል ግ ምገ ማጥያ ቄዎች አርብ ሚያዝያ 20
1. የ ሺህ ዓመቱን መጀመሪያ የሚያመለክተው የትኛው ክስተት እና እንዴት ነው? 2. የተሰሎንቄ ሰዎች ፍርሃት ምን ነበር? የጳውሎስ ቃላት የ ሚያጽናኑትስ እንዴት ነው? 3. የክርስቶስ ተስፋዎች የ ሚያጽናኑን እንዴት ነው? በተለይ የትኞቹ ናቸው? 4. ክፉዎች በክርስቶስ መምጣት ብሩህነት የጠፉት ለምንድን ነው? 5. የክፉዎች የመጨረሻ ጥፋት ምን ያህል ነው?
 <<    >>