Back to top

Sabbath Bible Lessons

ወንጌል እንደ ዮሐንስ መሠረት (ፍል ሁለት)

 <<    >> 

መቅድም

እንደ ዮሐንስ የወንጌል አጻጻፍ ከሌሎቹ (ሲኖፕቲክ ወንጌሎች ከሚባሉት) ከሦስቱ ወንጌሎች ዘግየት ያለ ቢሆንም አሁንም ግን በ1ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ነበር የተጻፈው። በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎች ጸሐፊው ሐዋርያው ዮሐንስ ነው የሚለውን እውነታ ለመቃወም ጥረት ሲያደርጉ፣ ከ150 ዓ.ም. በፊት መጻፉን ለመካድ ሞክረው ነበር። ተቺዎቹ የግኖስቲክ ፍልስፍናን እንደሚያንፀባርቅ እና ስለዚህ ግኖስቲሲዝም ለእምነት ከባድ ስጋት ከመሆኑ በፊት ሊጻፍ እንደማይችል ከሰሱ። (ግኖስቲሲዝም ከእምነት ይልቅ እውቀት ለመዳን ቁልፍ እንደሆነ በሚናገሩ የጥንት ኑፋቄዎች የፍልስፍና እና ሃይማኖታዊ ሥርዓት ነበር።) እንዲህ ያለው የተዛባ ክስ ውድቅ ተደርጓል።

በተቃራኒው፣ ውጫዊ መረጃዎች አራተኛው ወንጌል እንዳለ እና በ 115ኛው ዓ.ም፣ መጀመሪያ አከባቢ ይሰጠው የነበረውን ከፍተኛ ግምት እነደነበረ ይመሰክራል። ከእነዚህ ማስረጃዎች አንዱ ጥቂት የዮሐንስ ወንጌል ጥቅሶችን የያዘ ትንሽ የፓፒረስ (የጥንት ግብጻዊያን ወረቀት) ቁራጭ በተገኘበት ወቅት ነው። (ምዕራፍ 16፣ ቁጥር 31-33፣ 37፣ 38)፣ ራላንድስ ፓፒረስ (Rylands Papyrus) በመባል የሚታወቀው እና በተለምዶ P52 ተብሎ የተሰየመው፣ ይህ በፓሌኦግራፊያዊ (ስለጥንት ጽሑፎች በሚያጠና ሳይንስ) መረጃ መሠረት በ125ኛው ዓ. ም. አከባቢ የተጻፈ ማስረጃ ነበር፡፡ በ2ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በግብፅ የተገኘው ይህ ቁርጥራጭ፣ ለአራተኛው ወንጌል ጅማሮ እና መስፋፋት እንደ ተጨባጭ ማስረጃ ይቆጠራል። ይህንንም ታዋቂው የአዲስ ኪዳን ምሁር አዶልፍ ዴይስማን እንዲህ ሲል አረጋግጧል።

“የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው እጅግ በኋላ ነው የሚሉ ብዙ መላምቶች እንደ ሙቅ ቤት በፍጥነት ይደርቃሉ። የዮሐንስ ወንጌል በ2ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የነበረ ብቻ ሳይሆን ቅጂዎቹ ግብፅ ድረስ የደረሱ ስለመሆኑ በሪላንድ ፓፒረስ የተረጋገጠ ዘጋቢ ማስረጃ አለን። ስለዚህ የዚህ የወንጌል አመጣጥ መቼ ነበር የሚለውን ለመመለስ ወደ ቀደመው ዘመን መመለስ አስፈላጊ ነው።”—Deutsche Allgemeine Zeitung, Dec. 3, 1935.

የዮሐንስ ጽሕፈት በጥንቶቹ ክርስቲያኖች መካከል የተለየ ዓላማ ያለው ብቻ ሳይሆን፤ ከዘመናት ጀምሮ፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ለክርስቶስ ተከታዮች መንፈሳዊ መመሪያን፣ እርዳታንና ማበረታቻን ያመጣ ነው።

ጌታ “ለእኛ አዲስ የሆነ ብርሃን አለው፣ ይህም ደግሞ ከእውነት ቃል የሚወጣ የከበረ አሮጌ ብርሃን አካል ነው። እኛ ገና ወደ እኛ የሚመጡት የብርሃን ጨረሮች ብልጭታዎች ብቻ እያየን ነው። ጌታ ቀድሞ የሰጠንን ብርሃን በአግባቡ እየተጠቀምን አይደለም፣ እና በዚህም ተጨማሪ ብርሃን ለመቀበል ተስኖናል፤ በላያችን በበራው ብርሃን አልሄድንምና።

“እኛ እራሳችንን የሕጉ ጠባቂ ሕዝቦች ብለን እንጠራለን፣ ነገር ግን እጅግ ሰፊ የሆነውን የእግዚአብሔር ህግ መርሆዎችን አንረዳም። ቅዱስ ባህሪውን አንረዳም። የእውነት አስተማሪዎች ነን የሚሉ ብዙ ሰዎች ስለ ጌታ የሱስ ክርስቶስ ሕያው እውቀት ስለሌላቸው የአምላክን ሕግ በማስተማር ረገድ ስለሚያደርጉት ነገር ትክክለኛ ግንዛቤ የላቸውም።”—Selected Messages, bk. 1, pp. 401, 402.

የዚህ ወንጌል ቀጣይ ጥናት የሱስን የበለጠ እንድናውቀው ይርዳን!

የጄነራል ኮንፈረንስ ሰንበት ትምህርት ክፍል

 <<    >>