የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ
ለአለም ተልዕኮዎች
ዛሬ፣ ወቅታዊው መልእክት ይሰማል፡-
“በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የሚስዮናውያን መንፈስ መነቃቃት አለበት። እያንዳንዱ የቤተ ክርስትያን አባል በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የእግዚአብሔርን ሥራ እንዴት ማገዝ እንዳለበት ማጥናት አለበት። በሚስዮናዊነት መስኮች መከናወን ያለበት ሥራ አንድ ሺህኛው ክፍል ብቻ (በጣም ጥቅት) እየተሠራ ነው። እግዚአብሔር ሠራተኞቹን ለእርሱ አዲስ ግዛት እንዲጨምሩ ጠርቶአቸዋል። ታማኝ ሠራተኛን የሚጠብቁ ለም የሆኑ የሥራ መስኮች አሉ። አገልጋይ መላዕክት ደግሞ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ መንገድ ለመምህሩ አገልግሎት ከሚደክሙት እያንዳንዱ የቤተክርስቲያኑ አባላት ጋር ይተባበራሉ።
“በምድር ላይ ያለችው የክርስቶስ ቤተክርስቲያን የተደራጀችው ለሚስዮናዊነት (ወንጌልን ለማድረስ) አገልግሎት ዓላማ ነው፣ እና ጌታ መላው ቤተክርስቲያን አባላት ትላልቆቹም ሆነ ትናንሾች፣ ሀብታሞችም ሆነ ድሆች፣ የእውነትን መልእክት የሚሰሙበት መንገዶችን እና ዘዴዎችን ሲቀይስ ማየት ይፈልጋል። ሁሉም በሌላ አገር በአካል ተገኝተዉ እንዲሠራ አይደለም የተጠሩት፣ ነገር ግን ሁሉም የሚስዮናዊነትን ሥራ ለመርዳት በጸሎታቸው እና በስጦታቸው አንድ ነገር ማድረግ ይችላሉ።
“አንድቅን ክርስቲያን የነበረ፣ አሜሪካዊ ነጋዴ፣ ከሥራ ባልደረባው ጋር ሲነጋገር፣ እሱ ራሱ በቀን ሃያ አራት ሰዓት ለክርስቶስ እንደሚሠራ እንዲህ ሲል ይናገራል። 'በንግድ ግንኙነቴ ሁሉ ጌታዬን ለመወከል እሞክራለሁ። እድል ሳገኝ፣ ሌሎችን ወደ እሱ ለማሸነፍ እሞክራለሁ። ቀኑን ሙሉ ለክርስቶስ እየሰራሁ ነው። እና ማታ፣ እኔ ተኝቼ፣ ቻይና ውስጥ ለጌታዬ የሚሠራ ሰው አለኝ።'
አክሎም “በወጣትነቴ ሚስዮናዊ ሆኜ ወደ አረማውያን ለመሄድ ወሰንኩ። ነገር ግን አባቴ ሲሞት ለቤተሰቡ አስፈላጊዉን ነገር ለማሟላት ሥራ መሥራት ነበረብኝ። አሁን፣ ራሴ ከሚሄድ ይልቅ ሚስዮናዊ ሥራን እደግፋለሁ። በእንደዚህ ባለ የቻይና ግዛት ውስጥ ባለች ከተማ ሰራተኛዬ ይኖራል። እናም፣ እኔ ተኝቼ ሳለሁም፣ በተወካዬ አማካኝነት አሁንም ለክርስቶስ እየሰራሁ ነው።' ”—Testimonies for the Church, vol. 6, pp. 29, 30
በአለም ተልእኮዎች በኩል በማድረግ በሰማይ ባንክ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው። ከዚህ የተሸለ ጊዜ አይመጣም፣ እንዲሁም በኋላ ስንል ሊዘገይ ይችላል። ነፍሶች ያለ ክርስቶስ እና የወቅቱን እውነት ሳይሰሙ እየጠፉ ነው፣ እንዲሁም ጌታ በምድራችን ዙሪያ እንዲሰራጭ ውድ ብርሃንን በአደራ ሰጥቶናልና።
እባካችሁን በልግስና ስጡ፣ እናንተንና ስጦታችሁን ጌታ አብዝቶ ይባርክ። አናመሰግናለን!
የጀኔራል ኮንፈረንስ ሰንበት ትምህርት ክፍል መምሪያ