የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ
በፕሮክሆሮቭካ ፣ ሩሲያ ውስጥ ያለውን ቤተ ክርስቲያን እንደገና ለመገንባት
ሩሲያ በቆዳ ስፋት 6,612,073.2 ስኩዌር ማይል (17,125,191 ኪሜ 2 ) የሚሸፍን ሲሆን 147,000,000 ህዝብ አላት። ከ180 የሚበልጡ ብሔረሰቦች የተውጣጡ ሰዎች በዚህ ሰፊ ሀገር ውስጥ ይኖራሉ፣ ደግሞ ብዙ የተለያየ ሃይማኖትም አላቸው። ከነዚህ ኃይማኖቶች መካከል በጣም ታዋቂው የሩሲያ ኦርቶዶክስ (41.1%) ፣ ሌሎች የክርስትና እምነት ተከታዮች (6.3%) ፣ እስላም (6.5%) ፣ ኒዮፓጋን እና ቴንግሪስት (1.2%) ፣ ቡዲዝም (1.2%) ፣ አማኞች ያልሆኑ (25.2%) ፣ አምላክ የለሽ (13%)፣ የተቀሩት ምንም ዓይነት ሃይማኖት የላቸውም።
ከኤስዲአርም መጀመሪያ ጀምሮ፣ የዘላለም ወንጌል መልእክት በጣም አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እዚህ አልፏል። ብዙ አማኞች ከባድ ስደት ደርሶባቸዋል—እንዲሁም አንዳንዶቹ ለተሰቀለውና ከሙታን ለተነሳው አዳኝ የህይወት መስዋዕትነትም ከፍለው መስክረዋል።
በ1990ዎቹ መጨረሻ ላይ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራተኛ ከሚስቱ ጋር የሚስዮናዊነት ሥራ ለመፈጸም ወደ መካከለኛው ሩሲያ ሄደ። ከጥረታቸውና ከጸሎታቸው የተነሣ የምእመናን ቡድን ተደራጀ። ግን ለስብሰባና ለአምልኮ ቦታ አልነበራቸውም። በመጨረሻም በ 2006 በቤልጎሮድ ክልል የፕሮኮሆሮቭስኪ አውራጃ የከተማ አስተዳደር ማዕከል በሆነውና ሰፊ የብረት ማዕድን ክምችቶች ካላት ከኩርስክ ከተማ በስተደቡብ ምሥራቅ - በፕሶል ወንዝ አጠገብ፤ እህል፣ ቀይስር፣ የሱፍ አበባ እና ፍራፍሬ የሚመመረትበት አከባቢ በሆነዉ በፕሮኮሆሮቭካ ውስጥ አንድ ትንሽ ቤት ያለበት ቁራጭ መሬት አገኙ።
ብዙ መሰናክሎችን በተአምር አስወግዶ የዚህን ቤት ግዢ ሲባርክ የእግዚአብሔርን እጅ ከእኛ ጋር ሲሰራ አይተናል። በዚህ ክልል ውስጥ ያለው ሥራ እድገቱን የቀጠለ ሲሆን ብዙም ሳይቆይ ቤቱ በጣም ትንሽ በመሆኑ ሁሉንም የእግዚአብሔርን አምላኪዎች ለመያዝ በቂ ሊሆን አልቻለም፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከባለሥልጣናት ፈቃድ አግኝተን የ አምልኮ ቤት መገንባት ጀመርን። ወንድሞች መዋጮ አድርገዋል እንዲሁም ጠንክረው ሠርተዋል፣ ነገር ግን ይህንን ፕሮጀክት ለመጨረስ ጌታን የሚወዱ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ልግስና እርዳታ እንፈልጋለን። የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ በአጎራባች ክልሎች የወንጌል ስራን የበለጠ ለማዳረስ እድል ይሰጣል፣ ይህም የመጨረሻውን የድነት መልእክት ለማሰራጨት የብርሃን ማማ ይሆናል፡፡ በዚህ የአለም ክፍል ያለውን እውነትን ማዳረስ ሥራ ለመርዳት ልቡ ዝግጁ የሆነውን እያንዳንዱን ሰዉ ጌታ ይባርክ!
ከፕሮክሆሮቭካ ቤተክርስትያን እና ከሩሲያ ዩኒየን