እሁድ
፣ ሚያዚያ 26
1. ፍጥረትን ማስታውስ
ሀ. እግዚአብሔር በመጀመሪያ የፍጥረት ቀን ምን ፈጠረ? ዘፍጥረት 1:3-5
“በመጀመሪያ እግዚአብሔር በቃሉ ዓለምን ሲፈጥር በጨለማው ላይ ብርሃን ወጣ።”—The Desire of Ages, p. 464.
ለ. እንደ ተራ ተመልካች ሳይሆን ንቁ ተሳታፊ ሆኖ ዓለም ሲፈጠር ማን ነበር? ዘፍጥረት 1:1፣ 2፤ ዮሐንስ 1:1፣ 2፤ ቆላስይስ 1፡16
“በመጀመሪያ እግዚአብሔር በፍጥረት ሥራ ሁሉ ተገለጠ። ሰማያትን የዘረጋው፣ ምድርንም የመሰረተው ክርስቶስ ነው። . . . ምድርን በውበት፣ አየሩንም በዜማ የሞላው እርሱ ነው። በምድር ላይ፣ በአየር፣ በሰማይም ባሉት ነገሮች ሁሉ ላይ የአብ የፍቅር መልእክት ተጽፏል።”—Ibid., p. 20.
“ዓለማት ሁሉ በሕዋው ውስጥ እንዲቆዩ ያስቻላቸው እጅ በቅደም ተከተላቸውም በሥነ-ሥርዓት እንዲኖሩ አድርጐ የያዘ ያ እጅ በእግዚአብሔር ፍጥረተ-ዓለም ዩኒቨርስ ሁሉ ያሉትን ነገሮች እንቅስቃሴአቸው ሳይደክም እንዲቀጥል ያስተካከለ ያ እጅ ነው ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ የተቸነከረው።”—Education, p. 132.
ሰኞ
፣ ሚያዚያ 27
2. ብርሃን በምድረ በዳ
ሀ. የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ እንዴት ተመሩ? ዘጸአት 13:21፣ 22 በደመና ዓምድ እና በእሳት ዓምድ ውስጥ የተሸፈነውን መገኘት ግለጽ? ዘጸአት 13:21 (የመጀመሪያ ክፍል)፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 10፡1-4
“እግዚአብሔር ለሕዝቡ በተገለጠበት ጊዜ ሁሉ ብርሃን እርሱ የመገለጡ ምልክት በመሆን አገልግሎአል። በመጀመሪያ እግዚአብሔር በቃሉ ዓለምን ሲፈጥር በጨለማው ላይ ብርሃን ወጣ። የእሥራኤልን ሠራዊት ይመራ በነበረው የደመናና የእሳት አምድ ውስጥ ብርሃን ነበር።”—The Desire of Ages, p. 464.
ለ. ክርስቶስ ከእስራኤላዊያን ጋር በምድረ በዳ ስለነበረው መገኘት የተጻፈው ምንድን ነው—አምላክስ ለሕዝቡ ምን ጥበቃ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል? መዝሙር 105:39፤ ኢሳይያስ 4:5፣ 6
“ውብና አጽናኝ ከሆኑት የኢሳይያስ መልእክቶች ውስጥ አንዱ እንደሚነግረን በመጨረሻ ላይ ከክፉ ኃይላት ጋር በሚደረገው ታላቅ ፍልሚያ --የደመናና የእሳት አምድ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ጥንቃቄ እንደሚወክል ይነግረናል።”—Patriarchs and Prophets, p. 283.
ሐ. ክርስቶስ በሲና ራሱን የገለጠው እንዴት ነው—ሙሴና ሕዝቡስ ምን ምላሽ ሰጡ? ዘጸአት 19:16–18፤ 20:18፣ 19፤ ዕብራውያን 12፡21
“በተሰበሰበው ሕዝብ ፊት የጌታ ክብር እንደሚባላ እሳት ሆኖ በተራራው ጫፍ ላይ ተገለጠ፡፡ . . . የእግዚብሔር በስፍራው መገኘት ሕዝቡን በፍርሐት እንዲርድ ስላደረጋቸው፣ በእግዚአብሔርም ፊት በግምባራቸው ተደፉ።”—Ibid., p. 304.
“ሟች የሆነው የሰው ልጅ መሸከም እስከማይችል ድረስ የክርስቶስ መገኘት መገለጥ በጣም የከበረ ነበር። በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደው ሙሴ፣ 'እጅግ ፈርቻለሁ፣ እንቀጠቀጥማለሁ' ብሎ ጮኸ። አምላክ ግን ይህን ታላቅ ክብር እንዲቋቋምና ሕዝቡም ትኵር ብለው ማየት እስከማይችሉት ድረስ የሚያንጸባርቅ የብርሃኑ ነጸብራቅን ከተራራው ላይ ሲመለስ በፊቱ እስኪገልጥ ድረስ ብርታትን ሰጠው።”—Sons and Daughters of God, p. 225.
ማክሰኞ
፣ ሚያዚያ 28
3. ብርሃን በእግዚአብሔር ማደሪያ
ሀ. ክርስቶስ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ መገኘቱን ያሳየው እንዴት ነው? ዘጸአት 40:34፣ 35
“የእስራኤል ማሕበረሰብ የተጠናቀቀውን ቅዱስ ሥራ በታላቅ ጉጉት ተሰባስበው ተመለከቱ፡፡ ትዕይንቱን በታላቅ አክብሮትና እርካታ እያሰላሰሉ እያለ የደመና አምድ የመገናኛ ድንኳኑን ሸፈነ “የእግዚአብሔርም ክብር ማደሪያውን ሞላ”፡፡ መለኮታዊው ክብር በመገለጡ ሙሴ እንኳ ለጊዜው ሊገባ አልቻለም ነበር፡፡ ሕዝቡ የእጆቻቸው ሥራ ተቀባይነት በማግኘቱ በጥልቅ ስሜት ተዋጡ፡፡ ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው ደስታቸውን እንዳይገልጹ ጽኑ ፍርሃት አድሮባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔር እራሱን ዝቅ አድርጎ ከእነርሱ ጋር በማደሩ ጥልቅ የምስጋና ቃላት በማንሾካሾክ የልባቸውን ሐሴት በደስታ እንባ ገለጹ።”—Patriarchs and Prophets, pp. 349, 350.
“ከምህረት መክደኛው በላይ የመለኮትን ህልዎት አመላካች የሆነው አምላካዊ ክብር (Shekinah) ይገኛል፡፡ አምላካዊው ፈቃድ በኪሩቤል መካከል ተገልጾአል፡፡ መለኮታዊ መልእክት አንዳንድ ጊዜ ከሰማይ --ከደመና ውስጥ በድምፅ ለሊቀ ካኅኑ ይመጣ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ አምላካዊውን አዎንታን ወይም ተቀባይነት ለማሳየት በቀኝ በኩል ባለው መልአክ ላይ ብርሃን ያርፋል፡፡ በተቃራኒው አለመስማማትን ወይም ተቃውሞን ለማሳየት ደግሞ በግራ በኩል ባለው መልአክ ላይ ደመና ወይም ጥላ ያጠላል።—Ibid.
ለ. በኋላ ቤተ መቅደሱ ሲመረቅ (አገልግሎት ሲጀምር) ምን ተከሰተ? 2ኛ ዜና 7፡1
ለሙሴም በተራራው ላይ በኋላም በእግዚአብሔር ለዳዊት እንደ ተገለጠው ምሳሌ እጅግ ያማረ መቅደስ ተሠራ። ምድራዊው መቅደስ እንደ ሰማያዊ ተሠራ። ሰሎሞን በቃልኪዳኑ ታቦት አናት ላይ ካሉት ኪሩቤሎች በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ትልልቅ መላእክትን ሠራ፤ በታቦቱ ጫፍና ጫፍ ላይ አቆማቸው፣ ሁልጊዜም የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቁትን የሰማይ መላእክትን የሚያመለክቱ ነበር። የዚህን ማደሪያ ውበት እና ግርማ መግለጽ አይቻልም። በመገናኛው ድንኳን ውስጥ እንዳለ፣ የቃልኪዳኑን ታቦት በታላቅ ክብር፣ በቅዱስ ሥርዓት ተሸክመው በስፍራው ከቆሙት ከከበሩ ኪሩቤሎች ክንፎች በታች አስቀመጡት።
“ቅዱሳን መዘምራን በድምፃቸው በአንድነት በማዘም፣ በሁሉም ዓይነት የዜማ መሣሪያዎች፣ እግዚአብሔርን አመሰገኑ። በድምጻቸው በአንድነት እና በዜማ መሣሪያዎች፣ በመቅደሱ ውስጥ ሲዘምሩ፣ ድምጻቸውም በኢየሩሳሌም በአየር ላይ ሲሰማ፣ የእግዚአብሔር ክብር ደመና ቀድሞ ድንኳኑን እንደሞላው ሁሉ ቤቱን ሞላዉ።” ካህናቱም ከመቅደሱ በወጡ ጊዜ ደመናው የእግዚአብሔርን ቤት ሞላው፥ የእግዚአብሔርም ክብር ስለ ሞላ ካህናቱ ከደመናው የተነሣ ለማገልገል መቆም እስኪሳናቸው ድረስ የእግዚአብሔርን ቤት ሞልቶ ነበርና።”—Spiritual Gifts, vol. 4a, pp. 113, 114.
ረቡዕ
፣ ሚያዚያ 29
4. የወንጌል ብርሃን
ሀ. በዮሐንስ 8፡12 ላይ ያለው ታላቅ ተስፋ የሚሰጠን የክርስቶስ መልእክት የትኛው ነው?
“የዚህ እውነት መረዳት የነበራቸውና ያንን እውነት በማወጅ ተግባር ላይም የተሰማሩት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ መሪዎች አልነበሩም። እነዚህ [መሪዎች] ታማኝ ጠባቆች ቢሆኑ፣ በትጋትና በፀሎት ውስጥ ሆነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚመረምሩ ቢሆኑ ኖሮ፣ የሌሊቱን ሰዓት ባወቁት ነበር፤ በቅርብ ሊሆኑ ያላቸውን ክስተቶች ትንቢቶቹ ይገልጡላቸው ነበር። ይህንን ደረጃ ግን አልያዙም ነበርና መልእክቱ የተላለፈው በሌላ መደብ ነበር። … እግዚአብሔር ከሰጠው ብርሐን ራሳቸውን የሚያገሉ፣ ወይም ሊደርሱበት በሚችሉበት ደረጃ ሆነው ሳለ ቸል የሚሉት እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይተዋሉ።—The Great Controversy, p. 312
“ጌታ እጅግ የበለጸገ፣ የተትረፈረፈ፣ አስደሳች ተሞክሮ እንዲኖረን ሁሉንም ዝግጅት አድርጓል። ዮሐንስ ስለ ክርስቶስ ሲጽፍ፡- “በእርሱ ሕይወት ነበረች። ሕይወትም የሰው ልጅ ብርሃን ነበረች።” ሕይወት ከብርሃን ጋር የተቆራኘ ነው፣ ከጽድቅ ፀሐይ ብርሃን ካላገኝን፣ በእርሱ ምንም ሕይወት አይኖረንም፡፡ ነገር ግን ይህ ብርሃን ለእያንዳንዱ ነፍስ ተዘጋጅቷል፣ ጨለማ የሚመጣብን ከብርሃን ስንወጣ ብቻ ነው። የሱስ “የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሏል። በአለም ውስጥ ያለ ብርሃን፣ ህይወት ሊኖር አይችልም፡፡ ፀሀይ ብርሃኗን ባታወጣ፣ የሁሉም እፅዋትና እንስሳት ህይወት ሁሉ መጨረሻ ይመጣ ነበር። ይህ የሚያሳየው እራሳችንን በጽድቅ ፀሃይ ጨረር ስር ካላደረግን መንፈሳዊ ህይወት ሊኖረን እንደማይችል ነው። አንድ የአበባ ተክል በጨለማ ክፍል ውስጥ ካስቀመጥን ብዙም ሳይቆይ ይደርቅና ይሞታል፤ ልክ እንዲዚሁ እኛም ያለንን መንፈሳዊ ህይወት በጥርጣሬ እና በጨለማ ከባቢ አየር ውስጥ በመኖራችን እናጣለን።”—Sons and Daughters of God, p. 281.
ለ. ወደ የሱስ ስንዞር ምን ማረጋገጫ እናገኛለን? 2ኛ ቆሮንቶስ 3፡18
“ብሩህ ጨረሯ ውበቷን እና ቀጥ ያለ አቋሟን እንድትጠብቅ እንድረዳት አንዲት የአበባ ተክል ወደ ፀሀይ እንደምትዞር ሁሉ፣ እኛም የሰማይ ብርሃን በላያችን ላይ እንዲያበራ፣ ባህሪያችን እንዲያሳድግ እና ልባዊና በእግዚአብሔር ዓላማ ጸንቶ የመኖር ተሞክሮ እንድሰጠን የክርስቶስ ተከታዮች ወደ ፅድቅ ፀሀይ ዘወር ማለት አለብን።”—Ibid., p. 26.
“የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ ብቻ አላማዬ ያለ፣ ለተሰጠውም ብርሐን በትጋት ትኩረት የሚሰጥ እርሱ ታላቅ ብርሐን ይቀበላል። ወደ እውነት ሁሉ ይመራው ዘንድ፣ ለዚያ ነፍስ፣ ባለሰማያዊ ነፀብራቅ ኮከብ ይላክለታል።”—The Great Controversy, p. 312.
ሐሙስ
፣ ሚያዚያ 30
5. በልባችን ውስጥ ይበራል
ሀ. ጳውሎስ ስለ ዓለም ብርሃን በሰጠው አበረታች ማጣቀሻ እንዴት ልንበረታ እንችላለን? 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡6
“የእግዚአብሔር የከበሩ ሐሳቦች አእምሮአችሁን ይግዙ። ሕይወታችሁ ከየሱስ ሕይወት ጋር በተሰወሩ አገናኞች የተሰፋ ይሁን። በልባችሁ ውስጥ ከጨለማ ብርሃን እንዲበራ ወዶ ይብራ ያለው በየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን ሊሰጣችሁ ይፈልጋል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ነገሮች ወስዶ ያሳያችኋል፣ ወደ ታዛዥ ልብም ሕያው ኃይል እንዲሆኑ ያስተላልፋል። ክርስቶስ ወደ ማለቂያ የሌለው ጫፍ ይመራል። ከመጋረጃው ባሻገር ያለውን ክብር ትመለከታለህ፣ በዚህም ስለ እኛ ስለሚማልደው ስለእርሱ ብቃት ለሰዎች ትገልጣለህ።”—Christ’s Object Lessons, p. 149.
“በሰው ዘር የሚገለጠው የራሱ ክብር መንግሥተ ሰማያትን ወደ ሰዎች ያቀርባታል ስለዚህም የውስጡን ቤተመቅደስ የሚያስጌጠው ውበት አዳኝ በሚኖርበት ነፍስ ሁሉ ውስጥ ይታያል። ሰዎች በክርስቶስ ክብር ይማረካሉ። በዚህ መንገድ ከዳኑት ከብዙ ነፍሳት የውዳሴ እና የምስጋና ጅረት፣ እንዲሁም ክብር ወደ ታላቁ ሰጭ ይመለሳል።
“ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ። ኢሳ 60፡1 ሙሽራውን ለመገናኘት ለሚወጡት ሁሉ ይህ መልእክት ተሰጥቷል። ክርስቶስ በኃይልና በታላቅ ክብር ይመጣል። ከራሱና ከአብ ክብር ጋር ይመጣል። ከቅዱሳን መላእክት ሁሉ ጋር አብሮ ይመጣል። ዓለም ሁሉ በጨለማ በሚዘፈቅበት በዚያን ጊዜ፣ በቅዱሳን ማደሪያ ሁሉ ብርሃን ይሆናል። እነሱ የዳግም ምጻቱን የመጀመሪያውን ብርሃን ያያሉ። የማይደበዝዝ ብርሃን ከግርማው ይበራል፣ አዳኙ ክርስቶስ እርሱን ባገለገሉት ሁሉ ይደነቃል። ክፉዎች ከፊቱ ሲሸሹ የክርስቶስ ተከታዮች ደስ ይላቸዋል።”—Ibid., pp. 420, 421.
አርብ
፣ ግንቦት 01
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. መጽሐፍ ቅዱስ በፍጥረት ሥራ ስለ አብ፣ ስለወልድና ስለመንፈስ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
2. የሱስ ራሱን በምድረ በዳ ለሕዝቡ እንዴት እንደገለጠ ግለጽ።
3. የክርስቶስ ብርሃን በማደሪያው እና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የበራው እንዴት ነው?
4. የሱስ በቤተ መቅደሱ ሲመረቅ ራሱን ያሳየው እንዴት እንደሆነ ግለጽ።
5. ክርስቶስ ለእኛ እና በእኛ በኩል ራሱን የገለጠው እንዴት ነው?