እሁድ
፣ ግንቦት 17
1. የተሳሳተ መረዳት
ሀ. ደቀ መዛሙርቱ ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ሲያዩ የሱስን ምን ጥያቄ ጠየቁት? ዮሐንስ 9:1፣ 2
ለ. በአይሁድም ሆነ በደቀ መዛሙርቱ ስቃይን በተመለከተ ምን የተሳሳተ ሐሳብ ነበራቸው? ሰይጣንስ በዚህ የሚጠቅመው እንዴት ነው? ዮሐንስ 9፡34 (የመጀመሪያ ክፍል)።
“ሰው የኃጢአቱን ቅጣት በዚህ ዓለም እንደሚያገኝ በአይሁዶች ዘንድ በአብዛኛው ይታመንበት ነበር። እያንዳንዱ ደዌ የበሽተኛው ወይም የወላጆቹ ኃጢአት መቀጫ ነው ተብሎ ይታመን ነበር። ማንኛውም ስቃይየእግዚአብሔርን ሕግ በመተላለፍ እንደሚመጣ እሙን ነው፣ ነገር ግን ይህ እውነት ተዛብቷል። የኃጢአትና የኃጢአት ውጤት ሁሉ ጠንሳሽ የሆነው ሰይጣን ሰዎች ሕመምና ሞት ለኃጢአት መቀጫ እንዲሆን እግዚአብሔርበአምባገነንነት የወሰነው ነገር እንደሆነ አድርገው እንዲያምኑ አደረጋቸው። ስለዚህ ደዌ ወይም መቅሰፍት የደረሰበት ሰው ከደረሰበት ችግር በተጨማሪ የትልቅ ኃጢአተኛነትን ቀንበር መሸከም ነበረበት።
“ስለዚህ አይሁዶች የሱስን ችላ የሚሉበት መንገድ ተዘረጋላቸው። «እኛ ልንሸከመው የሚገባንን መከራና ሕማም» የተሸከመውን ጌታ አይሁዶች «ከእግዚአብሔር የተላከ ቅጣት...ከመከራና ከሕማም የማይለይ የሐዘን ሰው» እንደሆነ አድርገው ስለገመቱት እርሱን ላለማየት ፊታቸውን ሸፈኑ።”—The Desire of Ages, p. 471.
ሰኞ
፣ ግንቦት 18
2. የእግዚአብሔር ክብር እንድገለጥ
ሀ. የሱስ መከራንና ኃጢአትን በተመለከተ ብርሃንን የሰጠው በየትኛው ምላሹ ነው? ዮሐንስ 9፡3-5
“የየሱስ ደቀ መዛሙርት በኃጢአትና በስቃይ መካከል ስላለው ግንኙነት አይሁዶች እንደሚያምኑት ያምኑ ነበር። የሱስ የደቀ መዛሙርቱን ስሕተት ቢያርምም የሰውን ሰቃይ መንስኤ ሳይገልጽ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ግን ነገራቸው። በዚያ ስቃይ ምክንያት የእግዚአብሔር ሥራ እንደሚገለጥ ነገራቸው። «በዓለም ላይ ሳለሁ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ» አለ።”—The Desire of Ages, p. 471.
ለ. የሱስ ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ምን አደረገ? ዓይነ ስውሩ ከእሱ ጋር የተባበረው እንዴት ነው? ዮሐንስ 9:6፣ 7
“ይህን ብሎ የሱስ የዕውሩን ዓይኖች ቀባና ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሔዶ እንዲታጠብ ላከው፣ ሰውየውም ለማየት ቻለ። አብዛኛውን ጊዜ ለማወቅ ከመጓጓት የሚጠየቀውን ጥያቄ እንደሚመልሰው ሁሉ የሱስ በዚህ አኳኋን የደቀ መዛሙርቱን ጥያቄ በተግባር መለሰላቸው። ከደቀ መዛሙርቱ የሚጠበቀው የሰውየውን ሕመም በተመለከተ ማን ኃጢአት እንደሠራ ወይም እንዳልሠራ በተነሳው ጥያቄ ላይ እንዲከራከሩ ሳይሆን ዓይነስውሩን ሰው እንዲያይያደረገውን የእግዚአብሔርን ኃይልና መሐሪነት እንዲያስተውሉ ነው። የማዳኑ ኃይል የክርስቶስ እንጂ የጭቃው ወይም ሰውየው የታጠበበት መጥመቂያ አለመሆኑ ግልጽ ነው።”—Ibid.
ሐ. የዓይኑ ብርሃን የተመለሰለት ሰው ጎረቤቶች ምን ዓይነት ምላሽ እንደሰጡ ግለጽ፤ እንዲሁም በእሱና በጎረቤቶቹ መካከል የተደረገውን ውይይት አብራራ። ዮሐንስ 9፡8-12
“የዚያ ወጣት ጐረቤቶችና ዓይነስውር በነበረ ጊዜ ያውቁት የነበሩ ሁሉ «ይህ ሰው ያ ተቀምጦ ይለምን የነበረው አይደለምን?» አሉ። ዓይኖቹ ስለተከፈቱና ፊቱ ብሩህ ሆኖ በመለወጡ ሌላ ሰው ስለመሰለ በጥርጣሬ ተመለከቱት። ጥያቄው ከአንዱ ወደ ሌላው ተላለፈ። «አንዳንዶቹ አዎ እርሱ ነው! አሉ። ሌሎች ደግሞ እርሱን ይመስላል እንጂ እርሱ አይደለም አሉ።» ነገር ግን ትልቅ በረከት ያገኘው ሰው «እኔው ነኝ» በማለት ክርክሩን አቆመው።”—Ibid., pp. 471, 472.
ማክሰኞ
፣ ግንቦት 19
3. አንድ የመጣው ጥያቄ
ሀ. የአይሁድ መሪዎች ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ወደማን ወሰዱት? ለምንስ? በምን ቀን ነበረው ሰውየው የተፈወሰው? ዮሐንስ 9:13፣ 14
ለ. የፈሪሳውያንን ምላሽ ግለጽ። ዮሐንስ 9:15፣ 16
“ፈሪሳውያን የሱስን ኃጢአተኛ በማድረግ መሲሕ አይደለም ለማለት ተመኙ። እነዚህ ፈሪሳው ያን ዓይነስውሩን ሰው የፈወሰው ጌታ ሰንበትን እንዳቋቋመና የሰንበትንም አከባበር እንደሚያውቅ አልተገነዘቡም። ስለ ሰንበት አከባበር የሚያስደንቅ ቀናኢነት ያላቸው ይመስሉ ነበር፣ ይሁን እንጂ በዚያው ሰንበት ቀን ነፍስ ለማጥፋት ያቅዱ ነበር።”—The Desire of Ages, p. 472.
ሐ. ፈሪሳውያን ስለ ተፈወሰው ሰው እንዲመስከሩ የጠሩት ማንን ነው? ዮሐንስ 9:18፣ 19
“[ፈሪሳውያን]የሰውየውን ወላጆች ጠሩና «ዕውር ሆኖ ተወለደ የምትሉት ልጃችሁ ይህ ነውን?» ብለው ጠየቁዋቸው።
“ሰውየው ራሱ ዓይነስውር እንደ ነበረና በኋላም ለማየት እንደቻለ ቢነግራቸውም ፈሪሳውያኑ ግን ስሕተታቸውን ከማመን ይልቅ የሚያዩትን መረጃ ለመካድ መረጡ።”—Ibid
መ. ቀስሞ በውስጣችን የሰረጸ አመለካከት ካለን ሊያመጣብን ከምችለው ክፉ እንድንጠበቅ ማስጠንቀቂያ የተሠጠን እንዴት ነው? ምሳሌ 18፡13
“በሰሙት ነገር ላይ ተሞርኩዘው ሐሳቡን ተናጋሪው ለመግለጽ ከሞከረው ፈጽሞ በተለየ መልኩ በመቀበል በራሳቸው ውሳኔ ላይ የሚደርሱ ብዙዎች ናቸው። አንዳንዶች የራሳቸውን ጭፍን ጥላቻ ወይም አስቀድሞ የያዙትን አስተሳሰብ በመጠቀም ጉዳዩን ለዓላማቸው በተሻለ ሁኔታ እንዲስማማ አድርገው እንደፈለጉ ይገነዘባሉ።”—Testimonies for the Church, vol. 5, p. 695.
ረቡዕ
፣ ግንቦት 20
4. ማስፈራሪያ ገጠማቸው
ሀ. ፈሪሳውያን ዕውር ሆኖ የተወለደውን ሰው ወላጆች ለማስፈራራት የሞከሩት እንዴት ነው? እነሱስ ምን ምላሽ ሰጡ? ዮሐንስ 9:20፣ 21 ገለልተኛ መልስ የሰጡት ለምንድን ነው? ዮሐንስ 9:22፣ 23
“ፈሪሳውያን አንድ ምርጫ ነበር የቀራቸው፣ ያውም የሰውየውን ወላጆች ማስፈራራት ነበር። እውነተኛ በመምሰል «አሁንስ እንዴት ማየት ቻለ?» ብለው ጠየቁዋቸው። የክርስቶስን መሲሕነት የተቀበለ ሰው ለሰላሳ ቀናት ከምኩራብ ይገለላል የሚል ትእዛዝ ወጥቶ ስለነበር የሰውየው ወላጆች ለመከራከር ፈሩ። በነዚህ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ሕጻናት አይገረዙም፣ በጥፋ ተኛው ሰው ቤትም ለቅሶ አይለቀስም። ይህ ቅጣት እንደትልቅ መቅሰፍት ይቆጠር ስለነበር ቅጣቱ የተበየነበት ሰው ንስሐ ካልገባ ከዚያ የበለጠ ቅጣት ይደርስበታል። ለልጃቸው የተደረገው ትልቅ ድርጊት የሰውየውን ወላጆች በየሱስ እንዲያምኑ አድርጓቸው ነበር፣ ይሁን እንጂ «ይህ ሰው ልጃችን መሆኑንና ዕውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን። ነገር ግን አሁን እንዴት እንደሚያይና ዓይኖቹንም ማን እንዳዳነለት አናውቅም። እርሱን ጠይቁት። እርሱ በዕድሜው ሙሉ ሰው ስለሆነ ስለ ራሱ መናገር ይችላል» ሲሉ መልስ ሰጡ። ስለ ክርስቶስ መመስከር ስለፈሩ ኃላፊነታቸውን ከራሳቸው ወደ ልጃቸው አሳለፉ።”—The Desire of Ages, pp. 472, 473.
ለ. ማስፈራሪያ ሲደርስብን ምን ማስታወስ አለብን? መዝሙር 118:6
“ጸንታችሁ ቁሙ፣ ፈሪ ተብላችሁ ከመጠራት ብላችሁ የተሳሳተ እርምጃ አትውሰዱ። በተለይ ሕሊናህን እንድትሸጥ የሚያነሳሳህ ስላቅ፣ ዛቻና ወሬ እንድኖር በፍጹም አትፍቀድ።”—Fundamentals of Christian Education, p. 93.
“እውነተኛ ክርስቲያናዊ ባሕርይ በዓላማ ጽናት፣ በማይበገር ቆራጥነት፣ በምድርም ሆነ በገሃነም ሊቀየር ወይም ሊጠፋ የማይችል መሆን አለበት። ለዓለማዊ ክብር ስህበት የታወረ የማይሆን፣ ለዛቻ ደንታ የሌለው እና በተንኮል የማይነቃነቅ ያልሆነ ሁሉ ሳይታሰብ በሰይጣን ዘዴዎች ይወድቃል።”—Testimonies for the Church, vol. 4, pp. 543, 544.
የእግዚአብሔርን ህግ ከሚቃወሙት አድቬንቲስቶች በጣም ከባድ ተቃውሞ ይደርስብናል። ነገር ግን የኢየሩሳሌምን ግንብ እንደገነቡት ሰዎች በዘገባዎች፣ ውይይትን ወይም ክርክንር በሚፈልጉ መልእክተኞች፣ በማስፈራራት፣ በውሸት ሕትመቶች ወይም ሰይጣን ሊጠቀምባቸው በሚችልባቸው ማናቸውም ዘዴዎች ከሥራችን መዘናጋትና መደናቀፍ የለብንም።”—Ibid., vol. 3, p. 574.
ሐሙስ
፣ ግንቦት 21
5. ታሪክ ራሱን ይደግማል
ሀ. የአምላክን ትእዛዝ የሚጠብቁ ሰዎች የሚያጋጥሟቸውን ትዕይንቶችና ለትዕዛዙ ምን ምላሽ መስጠት እንዳለብን ግለጽ። ራእይ 12:17፤ የሐዋርያት ሥራ 4፡18-20
“ተቃርኖው (ተጋድሎው) ወደ አዳዲስ ስፍራዎች ሲገባና የሰዎችም አዕምሮ ወደ ተረገጠው ህገ-እግዚአብሔር እንዲያተኩር ሲጠራ፣ ሰይጣን በመታወክ የራወጣል። መልእክቱን የሚያጅበው ኃይል የሚያደርገው ነገር ቢኖር የሚቃወሙትን የበለጠ ማበሳጨት ይሆናል። በመንጎቻቸው ላይ እንዳያንፀባርቅ ብርኃኑን ለመጋረድ የቤተ ክርስቲያን ባለስልጣናት (ካህናት) ከሰው አቅም በላይ ሊባል የሚችል ጥረት ያደርጋሉ። ማድረግ በሚችሏቸው መንገዶች ሁሉ የእነዚህን አስፈላጊ ጥያቄ ውይይቶች ለመጨቆን ይማስናሉ። ቤተ ክርስቲያን የመንግሥታዊ ኃይልን ጽኑ ክንድ [እርዳታ] ትጠይቃለች፤ በዚህም ተግባር ላይ ጳጳሳዊያኑና ፕሮቴስታንቶች ያብራሉ። እሁድን አስገዳጅ የሚያደርገው ንቅናቄ እየተባና የበለጠ ቆራጥ እየሆነ ሲመጣ [የእግዚአብሔርን] ትዕዛዛት በሚጠብቁ ላይ ሕጉ እንዲሰለጥን ይደረጋል። በቅጣትና በእስር ማስፈራሪያ ይደርስባቸዋል። አንዳንዶቹም እምነታቸውን እንዲክዱ ማባበያ ይሆን ዘንድ ተጽዕኖ ፈጣሪ እርከኖች፣ ሽልማቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ይበረከቱላቸዋል። ነገር ግን የማያወላውለው መልሳቸው፣ ልክ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ሳለ፣ ሉተር ያቀረበው ጥያቄ (አቤቱታ) ይሆናል፦ “ስህተታችንን ከእግዚአብሔር ቃል ዘንድ አሳዩን።” በፍርድ ሸንጎዎች እንዲቀርቡ የሚደረጉ እነርሱ እውነትን ነፃ የሚያወጣ ጠንካራ መከራከሪያ ያደርጋሉ። ከሚሰሟቸው መካከል አንዳንዶቹም ሁሉንም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ጠብቀው እንደ እነርሱ ለመቆም ይመራሉ። በዚህ ሁኔታ እነዚህ እውነቶች በሌላ በምንም አይነት መንገድ ሊደርሳቸው የማይችሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ብርሐን ይደርሳቸዋል።”—The Great Controversy, p. 607.
ለ. ተቃውሞ ሲያጋጥመን ምንጊዜም ከግምት ውስጥ ማስገባት ያለብን ምንድነው? ዮሐንስ 9:39፤ የሐዋ. 4:33፤ ማቴዎስ 10፡28
(ደቀ መዛሙርት) በዛቻ ሊገቱ ወይም ሊፈሩ አይችሉም።”—The Acts of the Apostles, p. 48.
አርብ
፣ ግንቦት 22
የግል ግምገማ ጥያቄዎች
1. የአይሁድ መሪዎች በበሽተኞችና በሚሰቃዩት ላይ የሚፈርዱት እንዴት ነው?
2. ዓይነ ስውሩን ማንና ምን ፈወሰው?
3. የዓይነ ስውሩ ጎረቤቶች ለምን ግራ ገባቸው?
4. ወጣቱ ከተፈወሰ በኋላ ምን ሁኔታ አጋጥሞታል?
5. በወላጆቹ ላይ በደረሰው ዓይነት ወጥመድ እንዳልወድቅ ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው?