Back to top

Sabbath Bible Lessons

ወንጌል እንደ ዮሐንስ መሠረት (ፍል ሁለት)

 <<    >> 
  ሰንበት፣ ግንቦት 30፣ 2017

የመጀመሪያ ሰንበት ሥጦታ

በታሚል ናዱ፣ ህንድ ውስጥ ላሉ ሁለት አምልኮ ቤቶች

እንደ አርኪዮሎጂ (ታሪክ ቁፋሮ) ጥናት ማስረጃ መሠረት ከክርስቶስ ልደት በፊት 2600 ዓ.ዓ በከፍተኛ ከተሜነት የተስፋፋው የኢንዱስ ስልጣኔ ዛሬ ህንድ ተብሎ በሚታወቀው ክፍለ አህጉር ውስጥ ይገኝ ነበር፡፡ እዚህ ያለው ዋናው ሃይማኖታዊ ተጽእኖ ለረጅም ጊዜ ሂንዱዝም (79.8%)፣ ከዚያም እስልምና (14.2%)፣ ክርስትና (2.3%)፣ ሲክሂዝም (1.7%) እና ሌሎች ይጨምራል፡፡ ከ1920ዎቹ እና 1950ዎቹ ጀምሮ ከኤስዲኤ ሪፎርም እንቅስቃሴ ጋር የተወሰነ ግንኙነት እንዳለ ሪፖርቶች ቢኖሩም፣ ሰሜን ህንድ በኤስዲአርም አጠቃላይ ጉባኤ የውክልና ስብሰባ ላይ በይፋ የተወከለው በ1987 ነው።

በህንድ የደቡባዊው ዳርቻ - ታሚል ናዱ - በኢንዱስትሪ እና በእርሻ ውስጥ እንደ ሃይል ማዕከል ይቆጠራል። የጌታ ስራ እዚህ ላይ ከተመሠረተ ብዙ አመታትን አስቆጥሯል፣ ነገር ግን በዚህ ግዛት ውስጥ ከ72 ሚሊዮን በላይ የሆነዉን ሰፊውን ህዝብ ለማገልገል፣ ሰፊ ሥራ ያስፈልጋል።

በ2001 ዓ.ም በተካሄደዉ የሕንድ ሕዝብ ቆጠራ መሠረት የፓትቴዌራንፓቲ መንደር 7,744 ህዝብ ነበረው። አማካኝ የተማረ (ማንበብ የሚችል) ሰዉ በመቶኛ ሲሰላ 83% ነው፣ ከሀገር አቀፍ አማካይ 59.5% ከፍ ያለ ነዉ (ይህም ለሥነ ጽሑፍ ምቹ ነዉ)።

እዚህ አከባቢ ዋናው መተዳደሪያው ቡና ሲሆን ከዚያም ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ኮረሪማ፣ በርበሬ እና ሌሎች ቅመማ ቅመሞች ይከተላሉ። ፓላፓቲ ደግሞ 13,701 ህዝብ የሚኖርባት ትልቅ መንደር ነው።

ከፔሪያክላም የመጣ የወንጌል ሰባኪ ያላሰለሰ ሥራ፣ በተለይ በእነዚህ ሁለት አካባቢዎች የቤተ ክርስቲያን አባላት ቁጥር እንዲጨምር ረድቷል። የተለያዩ ተግዳሮቶች በመኖራቸዉ በክራይ ቤቶች ውስጥ ለመቀጠል በጣም አስቸጋሪ አድርገውታል፣ ስለዚህ አሁን ባሉበት ሁኔታ፣ በፓቲቬራንፓቲ እና በፓላፓቲ መንደሮች ውስጥ ያሉ ወንድሞች የራሳቸው የአምልኮ ቦታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ትንቢት መንፈስ ስለሕንድ በተላይ ሲናገር “በሚዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ወይም ስለ ፍቅሩ በክርስቶስ የተገለጠውን ያህል ሰምተው የማያውቁበት ቦታ እንደሆነ ይጠቅሳል። ይህንን እውቀት መቀበል መብታቸው ነው። የአዳኙ ምሕረት ከእኛ ጋር እኩል ይገባቸዋልና” ይላል።—Education, p. 263.

ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጌታ እዚህ እንዲበራ የብርሃን ማማዎችን ለመስራት በጎ ድጋፍ እንዲታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን። “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የማወጅና በእግዚአብሔር ህግ ላይ የተፈፀመውን ጥሰት በመጠገን፣ ለሚሰቃየው የሰው ልጅ ርህራሄን ማሳየት አለብን። ለእግዚአብሔር የላቀ ፍቅር ማሳየት አለብን፤ መታሰቢያውንም ከፍ ከፍ ማድረግ አለብን።”— Welfare Ministry, p. 32.

አናመሰግናለን፣ እንዲሁም ጌታ ስጦታዎቹንና ሰጭዎቹን ይባርክ!

ወንድሞቻችሁ እና እህቶቻችሁ ከፓትቬራንፓቲ እና ከፓላፓቲ

 <<    >>